Revenue Authority

የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ

የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅ/ጽ/ቤት በ16 ወረዳ ቅ/ጽ/ቤቶች፣በ5 ከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤቶች፣በ6 ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶችና ባጠቃላይ ዞን ማዕከል ጨምሮ በ28 ቅ/ጽ/ቤቶች የተደራጀ ሲሆን በስሩም 8(ስምንት) ዳይሬክቶሬቶች ይገኛሉ እነሱም፡-

  • የግብር ሕጎች ማስከበር ዳይሬክቶሬት
  • የታክስ ትምህርት ኮሙዩኒኬሽን እና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት
  • የየደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክቶሬት
  • ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና  መከታተያ ክፍል ቡድን
  • የዕቅድ ዝግጅት የአፈፃፀም ክትትል የለውጥ ስራ አመራርና መረጃ ዳይሬክቶሬት
  • የሰው ሀብት ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት
  • የታክስ መረጃ አሰባሰብ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እና የቴክኖሎጂ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • የሰው ሀብት መረጃ ስታቲክስ አቅርቦት ቡድን

የሴክተሩ ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች

ተልዕኮ

ሁለንተናዊ አቅሙ የተገነባ ተቋም እና የሰዉ ኃይል በማፍራት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ የተጣጣመ ሀገራዊ እና ክልላዊ የታክስ አስተዳዳር ሥርዓት በመገንባት፣ ፍትሀዊ፣ የላቀ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት፤ ታክስ በፍቃደኝነት የመክፈል ባህልን በማዳበር፤ የታክስ እና የገቢ ህግጋትን በማስከበር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ መሰብሰብ

ራዕይ

በ2022 ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ተገንብቶ ኢኮኖሚዉ ከሚያመነጨዉ ሀብት ሙሉ በሙሉ ገቢ ተሰብስቦ ለልማት ዉሎ ማየት

እሴቶች

  • አገልጋይነት
  • አገልግሎትን በጊዜና በጥራት በመስጠት በልጦ መገኘት
  • መሰጠት
  • ሙያና ክህሎትን ለተጨባጭ ውጤት መጠቀም /Professionalism/
  • ታማኝነት
  • ተጠያቂነት
  • በትብብርና በዉድድር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት

የተቋሙ የትኩረት መስኮች

  • ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አቅም ልማት
  • የአሰራር ልህቀት
  • ስትራቴጂያዊ አጋርነት ልህቀት
  • የህግ ተገዢነት አመራር ልህቀት
  • ዘላቂ የገቢ ዕድገት

ዕይታዎች

  • የተገልጋይ ዕይታ /Customer/
  • የፋይናንስ/የበጀት አጠቃቀም ዕይታ /Finance/
  • የውስጥ አሰራር ዕይታ /Internal Process/ 
  • የመማማርና ዕድገት ዕይታ /Learning and Growth/

በስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች የተጣሉ ግቦች

  • ግብ 1 – የሰው ሀብት የመፈጸም ብቃት ማሳደግ
  • ግብ 2 – ተቋማዊ የውስጥ የስጋት ስራ አመራርን ማሻሻል
  • ግብ 3 – የመረጃ ቴክኖሎጂ ሀብት እና አጠቃቀምን ማሻሻል
  • ግብ 4 – የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል
  • ግብ 5 – የባለብዙ ዘርፍ አካታችነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
  • ግብ 6 – የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም ልህቀትን ማረጋገጥ
  • ግብ 7 – የመረጃ አስተዳደር አፈፃፀምን ማሻሻል
  • ግብ 8 – የተጣጣመ የታክስ አስተዳደርን ማስፈን
  • ግብ 9 – የአሰራር ስርዓት አፈጻጸምን ማሻሻል
  • ግብ 10 – የባለድርሻ አካላት አጋርነትና ትብብር ማሻሻል
  • ግብ 11 – የህዝብ ግንኙነት እና ተቋማዊ ገጽታ ግንባታ ማሻሻል
  • ግብ 12 – የስጋት ስራ አመራር አፈጻጸምን ማሻሻል
  • ግብ 13 – የታክስ ማጭበርበር መከላከል አፈጻጸምን ማሻሻል                  
  • ግብ 14 – የታክስ ህግ ተገዥነት አፈፃፀምን ማሻሻል
  • ግብ 15 – የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነትን

የተቋሙ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች

  1. ታክስ በፈቃደኝነት የመክፈል ባህል ማሳደግ
  2. ዲጂታል የገቢ አስተዳደር ስርዓትን መገንባት
  3. ፍትሀዊነትን ማረጋገጥ
  4. የባለድርሻ አካላት ስትራቴጂያዊ አጋርነትና ትብብር ማሻሻል
  5. የዳበረ የስራ ባህል ማምጣት

የተቋሙ አድራሻዎች

የቢሮ ስልክ ቁጥር
  • 0113-30-01-17———የጽ/ቤቱ  ሀላፊ
  • 0113-30-26-10———የግብር ሕጎች ማስከበር ዳይሬክቶሬት
  • 0113-30-22-54  ——–የታክስ ትምህርት ኮሙዩኒኬሽን  እና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት
  • 0113-30-16-38———የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክቶሬት
  • 0113-30-01-79———ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን
  • 0113-30-09-20———የዕቅድ ዝግጅት የአፈፃፀም ክትትል የለውጥ ስራ አመራርና መረጃ ዳይሬክቶሬት
  • 0113-65-80-27———–የሰው ሀብት ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት
ፋክስ
  • 0113 30 22 53
ፖ.ሳ.ቁ
  • 177
መገኛ አድራሻ፡ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንፃ ስር ሁለተኛ ፎቅ

Comments are closed.