Plan and Economy

የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ

የክልሉ ፕላን ኮሚሽን በ2012 በጀት ዓመት በክልሉ ም/ቤት የክልሉን አስፈፃሚ መ/ቤቶች እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር180/2012 መሠረት የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በዚህም የማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት በዞን ደረጃ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በሚል ስያሜና  በወረዳ/ከ/አስተዳደር ደረጃ ደግሞ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በሚል የተደረጃ ሲሆን  ከዚህ በታች የተመለከቱት ዋና ዋና ኃላፊነትና ተግባራት ተሰጥተውታል ፡፡

  • የዞኑን/ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ይገመግማል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፡፡
  • የዞኑን /ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩ መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል ይገመግማል ያስፀድቃል፡፡
  • የዞኑን/ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል  ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፡፡
  • አመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል ‘ለዞኑ ም/ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፡፡
  • የዞኑን/ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩ ኢኮኖሚ ማህበራዊና መልከአ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል ‘ ያደራጃል ‘ ትንተና በማድረግ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፡፡
  • የዞኑን /ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩ ማህበራዊ ‘ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልከአ ምድራዊ ገፅታን የሚያሳይ  ካርታ ያዘጋጃል፡፡
  • የዞኑን/ወረዳውን/ከ/አስተዳደሩየሥነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አካያ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፡፡
  • በሥነ ህዝብ ጉዳዮች ዙሪያ የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎችን ያካሂዳል፡፡
  • በክልሉ የሚዘጋጀው የአምስት ዓመት ሰነድ መነሻ በማድረግ  የስነ ህዝብ ፕሮግራም በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ ህዝብ ም/ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ውይይት ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ተቋሙ ከላይ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት በብቃትና በውጤታማነት ለመወጣት በሶስት ዋና ዋና ተልዕኮ ተኮር ዳይሬክቶሬቶች ማለትም የፕ/ዝ/ክ/ግ ዳይሬክቶሬት፣ የስነ-ህዝብና ልማት ዳይሬክቶሬት እና ፊዚካል ጂኦግራፊ ጥናት መረጃ ትንተናና ስርጭት ዳይሬክቶሬት እና በሶስት የወል ዳይሬክቶሬቶች እነዚህም የሰው/ሀ/ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ፣ የል/ዕ/ዝ/ክ/ግ ዳይሬክቶሬት እና የሰው ሃብት መረጃ ስታትሰቲክስ ዳይሬክቶሬት  በሚል ተደራጅቷል፡፡

የሴክተሩ ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች

ተልዕኮ

በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መለስተኛ ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በዞኑ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው  ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡

ራዕይ

ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የዞኑ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ  ማየት፡፡

እሴቶች

  • ቆጣቢነት
  • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
  • ፍትሃዊነት
  • ውጤታማነት
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት
  • ተቆርቋሪነት
  • ቀልጣፋ አገልገሎት
  • በእቅድ መመራት
  • ሕጋዊነት

የተቋሙ የትኩረት መስኮች

የትኩረት መስክ 1፡ የልማት ዕቅድ እና የስነ-ሕዝብ ጉዳዮች

ውጤት

በሁሉ አቀፍ የተቀናጀ አሳታፊ የልማት እቅድ ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ልማት ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ ስርዓትና ከኢኮኖሚው ጋር የተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር እድገት ፈጣንና ዘላቂነት ያለውን የዞኑን ልማት ለማምጣት የህዝብ፣የመንግስትና የልማት አጋሮች ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው። የእነዚህ አጋሮች ልማታዊ እንቅስቃሴ በየደረጃው አሳታፊ በሆነ ስልት እቅድ በማዘጋጀት ክትትልና ግምገማ በማካሄድና እንዲሁም ግብረ-መልስ በመስጠት ሁለገብ ልማቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ መምራት እንደሚቻል በቀደምት ልምዶቻችን የተረጋገጠ ስለሆነ የልማት ዕቅድ እና የስነ-ሕዝብ ጉዳዮች እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ እንደ አንድ የሴክተሩ የትኩረት መስክ ሆኖ ተመርጧል፡፡

የትኩረት መስኩ በዋናነት ያቀፋቸው አንኳር ተግባራት
  • በዞኑ የተገኘውን ሐብት በእቅድ የመምራትና የመከታተል
  • የመንግስት ወጪ ፕሮግራሞች
  • የሐብት ማከፋፈያ ቀመር ዝግጅት
  • የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር
  • የዕቅድ ክንውን ክትትል ፣ ግምገማ እና ስልጠና
  • የስነ-ሕዝብስራዎችን ማስተባበርና መተግበር
  • በስነ-ሕዝብ ጉዳይ ላይ የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ማካሄድ
  • የስነ-ሕዝብ ፕሮግራም ሰነድና ልዩ ልዩ መረጃዎችን ማዘጋጀት

ትኩረት መስክ 2፡  ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና መልክአምድራዊ መረጃ ትንተና እና ስርጭት

ውጤት

ወቅታዊ፣ ተአማኒነት ያለው፣ የተሟላና ተደራሽ የሆነ መረጃ፤ የልማት መረጃ ለአንድ አገር ኤኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የሚኖረው ድርሻ ወሳኝ ነው:: በተክክለኛ መረጃ ላይ ያልተደገፈ የልማት ፖሊሲና ዕቅድ የህብረተሰቡን ፍላጎት የማያረካና ችግሩን የማይፈታ ነው። ስለዚህ ዘላቂና ፈጣን ልማት ለማምጣት አስተማማኝና ወቅታዊ የልማት መረጃ ማግኘት ያስፈልጋል:: በመሆኑም ከዘርፉ አስፈላጊነትና ከልማትም ጋር ካለው ትስስር አኳያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልክአ-ምድራዊ መረጃ ትንተናና ስርጭት ሌላው የትኩረት መስክ ሆኖ ተመርጧል::

የትኩረት መስኩ በዋናነት ያቀፋቸው አንኳር ተግባራት
  • የመረጃ ዳታ-ቤዝ መጠቀምና የተገልጋዩችና የባለድርሻ አካላት ፍላጎት ማጥናት
  • የዞኑን የተፈጥሮ ሀብት ፣ መልክዓ-ምድራዊና የሶሽዮ ኢኮኖሚ ገጽታና ሥርጭታቸውን የሚገልጽ መረጃን መተንተንና ማሰራጨት
  • መረጃዎችን መሰብሰብ ፣ ማጥራት ፣ ማደራጀት ፣ መተንተን በድረ-ገፅና /web- site/ በሕትመት ለተገልጋዮች ማሰራጨት
  • የልማት ክፍተት ሊለዩ የሚችሉ መረጃዎችን ማሰባሰብና ማደራጀት

የተቋሙ የልማት ዕቅድ ግቦች

  • ግብ 1 – ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ
  • ግብ 2 – ፍላጎትን መሰረት ባደረገ የልማት ዕቅድ ዝግጅት፤ ክትትልና ግምገማ በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ
  • ግብ 3 – የስታትስቲክስና መልካ-ምድራዊና የካርታ መረጃን ተደራሽ በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ
  • ግብ 4 – የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን መጨመር
  • ግብ 5 – የዞኑን የመካከለኛ ጊዜ ማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ማዘጋጀት
  • ግብ 6 – የዞኑን የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ሰነድ ዝግጅት ማጠናቀቅና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማሳተም ለተተቃሚዎች ማሰራጨት
  • ግብ 7 – ዞናዊ የካፒታል ኘሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ በዓመት ሁለት ዙር ማከናወንና  ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ
  • ግብ 8 – በዞኑ የሚተገበሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከትገበራ በፊት የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ማካሄድና ፍትሃዊ ስርጭቱን ማረጋገ
  • ግብ 9 – የዞኑን የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ የአፈጻጸም ማንዋል ማዘጋጀት
  • ግብ 10 – የስታቲስቲክስና መልከ-ዓምድር መረጃዎችን አሰባሰብ ዝግጅትና አቅርቦት በሁሉም መዋቅሮች በማጠናከር የተጠቀቃለለ ዘናዊ ሰነድ ማዘጋጀት
  • ግብ 11 – የስታቲስቲከሰና መልከዓ-ምድር መረጃ አስተዳደር ስርአቱ የጥራት ደረጃዉን መፈተbና ማጠናከር
  • ግብ 12 – የሴክተሩ የመረጃ አደረጃጀት ስርአት ለማሻሻልና የዞኑን መረጃ ክፍተት ለመሙላትና የዞኑን መንግሰት ፖሊሲ ጉዳይ ጋር የተያያዙ መለስተኛ ጥናቶችን ማከናወን
  • ግብ 13 – የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀም መሻሻል
  • ግብ 14 – የዞኑን የተፈጥሮ ሀብት የልማት ፖተንሻል የሚያመላክቱ የካርታ መረጃና ትንተና ማዘጋጀት
  • ግብ 15 – የስነ ህዝብና ልማት ጉዳዮችን ማስተባበርና መተግበር
  • ግብ 16 – በዞናዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ዙሪያ ለወረዳዎችና ከ/አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠና ማዘጋጀት
  • ግብ 17 – በፕሮጀክት ዝግጅት አዋጭነት ጥናት እና በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ለሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት
  • ግብ 18 – የሰው ሀብት ብቃትና ተነሣሽነትን የማስፈጸም አቅም ማሣደግ

የተቋሙ አድራሻዎች

  • የቢሮ ስልክ ቁጥር011 365 94 72
  • ፋክስ እና ኢሜይል ለጊዜው የሌለን ሶሆን ሲኖረን ወዲያውኑ የሚናሳውቅ ይሆናል

Comments are closed.