Culture & Tourism

የጉራጌ ዞን  ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል

  • በዞኑ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ ቅርሶችና እሴቶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁ
    ለሣይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲውሉ ያደርጋል፤
  • በዞኑ የሚገኙ ቋንቋዎች እንዲጠኑ፣ ሥነ-ጽሑፎቻቸው እንዲዳብሩና እንዲስፋፉ ያደርጋል፤
  • የትርጉም አገልግሎትና የአስተርጓሚነት ሙያ ዕውቀት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ
    የሚያደርጉ ተግባሮችን ያከናውናል፤ ደረጃውን የጠበቀ የሥራ ቋንቋ አጠቃቀም
    እና የትርጉም አገልግሎት እንዲኖር ይደግፋል፣ ክትትል ያደርጋል፤
  • በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተፅእኖ ሳቢያ ማኀበራዊ እድገትን የሚያጓትቱ
    አመለካከቶችን፤ እምነቶችንና ልማዳዊ አሰራሮችን የመለወጥ ተግባሮች
    ያከናውናል፤
  • በዞኑ ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ባህሎች እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  • በባህል ዘርፍ የሕዝቡን ተሳትፎ ተቋማዊ መሠረት ለማስያዝ የባህል ተቋማት
    እንዲስፋፉ ያደርጋል፤
  • የዕደ ጥበብ፣ የኪነ ጥበብና የሥነ-ጥበብ ሥራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ ለልማቱ
    የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የዘርፉን መረጃዎች በዘመናዊ መንገድ
    እንዲደራጁ ያደርጋል፣ ተደራሽነቱንም ያረጋግጣል፣
  • በዘርፉ ውጤታማ የፈጠራ ሥራዎችን ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና
    ማበረታቻ የሚሰጥበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣
  • በዞኑ የፊልም ተውኔት ጥበብ ሥራዎች የሚያድጉበትን አግባብ ያመቻቸል፣
  • በዞኑ የቱሪዝም መስሕቦችና መልካም ገፅታ ያስተዋውቃል፤ ቱሪዝም በዞኑ
    እንዲስፋፉ ያበረታታል፤
  • በዞኑ ቱሪስት መስሕቦች ተለይተው እንዲታውቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው
    እንዲለሙና እንዲደራጁ፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንዲስፋፉ፣
    የየአካባቢው ማኀበረሰብም ከቱሪዝም ጥቅሞች ተካፋይ እንዲሆን የሚደረግበትን
    አግባብ ያመቻቻል፤
  • በዞኑ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው
    እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ በሃገር
    አቀፍ ደረጃ በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት የዞኑ
    ቅርሶች በአለም አቀፍ ቅርስነት የሚመዘገቡበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት
    ጋር ያመቻቻል፣
  • የባህልና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን
    ይቆጣጠራል፣
  • በቱሪዝም የሠመረ አገልግሎት እንዲኖር የቱሪስቶችም ደህንንት እንዲረጋገጥ
    የሚያስፈልገው የብዙ ወገኖች የሥራ ቅንጅት እውን እንዲሆን ለሚፈጠሩ የጋራ
    መድረኮች በማዕከልነት ያገለግላል፣
  • በሰው ኃይል ሥልጠናና በሙያ ምክር አገልግሎት አማካይነት የባህል፣ የስፖርትና
    የቱሪዝም ሴክተርን የማስፈጸም አቅም ይገነባል፣
  • የባህል፣ ስፖርትና ቱሪዝም መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ያሰራጫል፡፡
  • ህዝቡን በስፖርት ለሁሉምና ባህላዊ ስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደርጋል፣
  • የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራትና ብቃትን ለማሳደግ የስፖርት ትምህርት፣ ሥልጠናና ምርምር ተቋሞች የሚቋቋሙበትን ሥልት በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችንና የስፖርት ማበልጸጊያ ማዕከላትን ያስፋፋል፤
  • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የስፖርት ህክምና አገልግሎት ያደራጃል፤
  • በስፖርት አበረታች መድሃኒቶችና ዕፆች መጠቀምን ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣
  • ውድድሮችንና ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት የስፖርቱ ዘርፍ የገቢ መሠረቶችን ያሰፋል፣ የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያሳድጋል፣
  • የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት በወጣ መመሪያ መሰረት የሚቋቋሙ የስፖርት ማህበራትን ይመዘግባል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፡፡
  • በሥራ ላይ ባሉ የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች ስፖርትን በሚመለከት ለወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባሮች በሙሉ ለባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በአዋጅ ተሰጥተዋል፡፡

የሴክተሩ ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች

ተልዕኮ

በዞኑ በዋናነት የሚገኙ የጉራጌ፣የቀቤና እና የማረቆ ብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶች፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን/ቅርሶችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ፤ የህብረተሰቡን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን በማዘመን ዞናችን በስፖርት ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በህብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በላቀ ደረጃ በማሳደግ እና መልካም ገጽታ በመገንባት የዞናችንና ብሎም የአገራችንን ዘላቂ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ብልፅግና ማረጋገጥ፡፡

ራዕይ

በ2022 የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የዞኑ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ፣

እሴቶች

  • ብዝሀነትን ማክበር
  • እንግዳ ተቀባይነት
  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • የላቀ አገልግሎት
  • አሳታፊነት
  • ህዝባዊነት
  • ፈጠራን ማበረታታት
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት
  • የአገልግሎት ጥራት
  • በቡድን መስራት

ዋና ዓላማ

ሴክተሩ ለዞኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ብልጽግና የሚኖረውን ጉልህ አስተዋጽኦ በማጎልበት የዞኑን ብሔረሰቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፣

ዝርዝር ዓላማዎች

  • የጉራጌ፣የቀቤናና የማረቆ ብሔረሰቦችን ቋንቋ፣ ሥነ ጥበብ፣ ባህል፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በማጥናት፣ በዘለቄታዊነት በመጠበቅ፣ በመሰነድና በማልማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳቸውን ማሳደግና ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ፣
  • የጉራጌ የቀቤና እና የማረቆ ብሔረሰቦችን የባህል ዕሴቶች በማጥናትና በማልማት የህዝቦችን የእርስ በርስ ትስስርና አብሮነትን ማረጋገጥ ፣
  • የባህልና የቱሪዝም ኢንዱስትሪን በማሳደግ የሥራ ዕድልን ማስፋፋትና የቱሪስት ፍሰትንና ገቢን ማሳደግ፣
  • የማህበረሰብ ስፖርትን በየደረጃው እንዲስፋፋ በማድረግ፣ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋንና ብቁ ስፖርተኞችን በማፍራት ዘርፉ ለሰላም፣ ለአንድነትና ለብልጽግና የሚኖረውን ፋይዳ ማጎልበት ነው፡፡

የተቋሙ የልማት ዕቅድ ግቦች

  • ግብ1፡ ያደገ የቅርስ እንክብካቤና ጥበቃ ፣
  • ግብ 2፡ ያደገ የቋንቋ ልማትና አጠቃቀም ፣
  • ግብ 3፡ ያደገ የባህል እሴቶች ልማትና አጠቃቀም ፣
  • ግብ 4፡ ያደገ የባህል ኢንዱስትሪ ልማትና የገበያ ትስስር ፣
  • ግብ 5፡ ያደገ የተፈጥሮ መስህቦችና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ጥበቃና ልማት ፣
  • ግብ 6፡ የአገር ውስጥ የጉብኝት ባህልን ማሳደግ
  • ግብ 7፡ ያደጉና የበቁ የሴክተሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣   
  • ግብ 8፡ የጎለበተ የመዳረሻና መስህብ ልማት፣
  • ግብ 9፡ የተስፋፋና ያደገ የግብይትና ፕሮሞሽን ስራ፣
  • ግብ 10፡ ያደጉና ውጤታማ የሆኑ የውድድር መድረኮች
  • ግብ 11. ህጋዊነታቸው የተረጋገጠና ተደራሽ የሆኑ የስፖርት ማዘዉተሪያ ስፍራዎችና ማዕከላት
  • ግብ 12፡ ያደገ የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ፣
  • ግብ 13፡ ያደገ በዘርፉ የተፈጠረ የስራ እድልና ገቢ ፣
  • ግብ 14፡ የጎለበተ የባለድርሻና አጋር አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ፣
  • ግብ 15፡ የጎለበተ ብዝሀነትና አቃፊነት፣
  • ግብ 16፡የጎለበተና የዘመነ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት፣
  • ግብ 17፡ ያደገ የሴክተሩ የትምህርትና ስልጠና ስርዓት፣
  • ግብ 18፡ ያደጉ የስፖርት አደረጃጀቶች፣
  • ግብ 19፡ ያደገ የሴክተሩን የጥናትና ምርምር ስራዎች፣
  • ግብ 20፡ ያደገ ተቋማዊ የመፈጸምና ማስፈፀም አቅም፣
  • ግብ 21፡ የተሻሻለ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች የአሰራር ስርዓት

የተቋሙ አድራሻዎች

  • ስልክ: 011 365 80 51/ 011 365 80 53/ 011 365 80 54/ 011 365 80 55/ 011 365 80 58/ 011 365 80 59/ 011 365 86 84/011 365 86 24
  • ፋክስ: –
  • ኢሜል: –

Comments are closed.