በሀገሪቱ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትና ከውጭ ሀገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የምግብ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እንደሚሰሩ በጉራጌ ዞን በተለያዩ የስራ ዘርፎች በልማት ቡድን የተደራጁ ሴቶች ገለጹ።

የሴቶች የልማት ቡድን አደረጃጀት የሴቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸው እንዳሳደገላቸው የዞኑ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። አሁን ላይ በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለዉን የኑሮ ዉድነትና በተለያዩ ምርቶች ላይ የሚስተዋለዉን የዋጋ ግሽበት ለማስቀረት የሴቶች…

Continue reading

የደቡብ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሺንሺቾ እና ቡኢ ከተሞች በባስኬት ፈንድ ለሚያስገነባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች የግንባታ ስምምነት ፊርማ ስነሥርዓት ከሁለት ውሃ ሥራ ተቋራጮች ጋር ፈፅሟል፡፡

በስምምነት ፊርማ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከመንግስትም ሆነ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች…

Continue reading

በነዳጅ ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአነስተኛና መካከለኛ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉም የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የታሪፍ ማሻሻያው በመመሪያው መሠረት ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተጠቁሟል ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩም ይታወቃል ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በትራንስፖርት ዋጋ ላይ የታሪፍ ጭማሪ መደረጉም…

Continue reading

በስነጽሁፍ የዕድሜ ዘመን ተሸላሚ ፤ ሃያሲ፣ ደራሲ እና ተርጓሚ የክብር ዶክተር ሳህለ ስላሴ ብርሃነ ማርያም የምስጋና ስነስርዓትና በደራሲው የተዘጋጀ ‹‹የሺንጋ መንደር›› የተሰኘ መጽሃፍ ርክክብ መርሀ ግብር በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የታደሙት የዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት ካውንስል አባላት፤ከዞን ትምህርት መምሪያ የተውጣጡ የትምህርት ባለሙያዎች፤ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ከአባ ፍራንሷ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ 50 ተማሪዎች ሲሆኑ…

Continue reading