የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ወረዳ ከ76 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያስገነባው የሚገኘው የጉስባጃይ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ የክልሉ ርዕሰ መንግስት ገለፀ ፡፡

የትምህርት ቤቱ የግንባታ ሂደት የደረሰበት ደረጃ በኦሮሚያ ክልል፣ በጉራጌ ዞንና በእነሞርና ኤነር ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎብኝቷል። በጉበኝቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን…

Continue reading

በ2014 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ከ103 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት እንደሚለማ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በተቀናጀና የተፋሰስ ልማት በእንስሳትና አሳ ሀብት እና በቡና ልማት ላይ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ። የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ እንደተናገሩት ባለፉት አመታት…

Continue reading

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባም የጉራጌ ዞን አስተዳደር አሳሰበ ።

የዞኑ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2014 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ መገምገሙን ተመልክቷል። በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል እንደገለጹት…

Continue reading

የጉራጌ ማህበረሰብ አንድነት ይበልጥ በማጠናከር የህብረተሰቡ ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ አስተዳደር አስታወቀ።

የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ ተካሄደ። በዚህም ጉባኤ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ በጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ በጉባኤው ተሳታፊዎች ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።…

Continue reading