ባለፉት አመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ከማሳደጉ ባሻገር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ ።

ዞናዊ የ2014 ዓመተ ምህረት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ በጌታ ወረዳ በቋንጤ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል። በተፋሰስ እወጃዉ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የግብርና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ካሳ…

Continue reading

ወጣቱ ማህበረሰብ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፎች ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊነት ውስደው መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

መምሪያው የወጣቶች የማካተት መመሪያ ወይም ጋይድ ላይን ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ አብዶ…

Continue reading

በየደረጃው ህዝቡ የሚጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመፍታት ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የአቤቱታና ቅሬታ ሰሚ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የህዘብ እምባ ጠባቂ ተቋም ገለፀ ።

ተቋሙ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የአቤቱታ እና ቅሬታ ሰሚ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መስጠቱን ተመልክቷል ። በኢትዮጵያ የህዘብ እምባ ጠባቂ…

Continue reading