ዜጎች የሚጠይቁትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የሚመጥን የአገልግሎት ስርአት በመዘርጋት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርሺስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በዞኑ ለሚገኙ ለቀበሌ ስራ አስኪያጆች የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ባለሙያዎች በሴክተር ተኮር ሪፎርም አተገባበር፣ በመሰረታዊ ስራ አመራር፣ በስነ-ምግባርና በመልካም አስተዳደር እቅድ አስተቃቀድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል። የጉራጌ…

Continue reading

በየደረጃው በሚገኙ ምክር ቤቶች የተወከሉ ህዝብ ተወካዮች የክትትልና ቁጥጥር ስራቸው በማጠናከር የህዝብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ምክርቤት ገለፀ።

በዞኑ በ2013 ዓመተ ምህረት በተካሄደው 6ኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክርቤቶች ተወክለው የገቡ የህዝብ እንደራሴዎች በየደረጃው ከወከላቸው ህዝብ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው ዛሬ ከህዝብ በተነሱ ጥያቄዎች ከዞኑ አስፈፃሚ…

Continue reading

በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ1ሺህ 8 መቶ 45 ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

በእዣ ወረዳ በአጓይተረህ ቀበሌ ወጣቶች ተደራጅተው በ13 ሄክታር መሬት ያለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተጎብኝቷል። በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በጉብኙቱ ወቅት እንደገለፁት…

Continue reading

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዕቅድ አቅዶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ የአስር አመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሂዷል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በውይይቱ ተገኝተው እንደተናገሩት በዞኑ የታቀደውን የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ…

Continue reading