የህግ ታራሚዎች በእውቀትና በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው እንዲወጡ ለማድረግ የትምህርትና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለፀ ።

በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የልማት ስራዎች እያከናወኑ መሆኑም ተጠቁሟል። የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ተቋም ለሚገኙ…

Continue reading

በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በፈረጀቴ ጎጥ 42 ቤቶች ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ መድረሱ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ።

በጉራጌ ዞን በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በፈረጀቴ ጎጥ ልዩ ስሙ ሀጅ አጂቦ መንደር ውስጥ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በመንደሩ የነበሩ 42 ቤቶችን ከነሙሉ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልፆል። በአደጋው ሰለባ የሆኑ…

Continue reading

በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የአርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባር ከመሆኑም በሻገር ከውጭ የሚገባውን እርዳታ ማስቀረት እንደሚችል የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳደር ገለጸ ።

በበጋ መስኖ ስንዴ እና በመደበኛ መስኖ 3 ሺህ 5 መቶ 97 ሄክታር መሬት መልማቱም ተግልጿል። የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር በመስክ ጉብኝቱ ላይ እንዳሉት የውኃ አማራጮችን በማስፋትና የማህበረሰቡን…

Continue reading

የጉራጌ ብሄር ባህላዊ ዕሴት በመጠበቅና በልማት በማስተሳሰር አንድነቱን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አስታወቀ።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ የብሔሩ ተወላጆች በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የጉልባማ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ጀማል ጉባኤው በንግግር ሲከፍቱ እንደገለጹት የልማት ማህበሩ…

Continue reading