ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ የባለሀብቱ ተሳትፎና ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በባለሀብቱ በአቶ ወርቁ ሽራጋ የተገነባው የአንዘቸ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ መሆኑንም ተጠቁሟል፡፡ የትምህርት ቤቱ ግንባታ አስመልክቶ ባለሀብቱ አቶ ወርቁ ሽራጋ እንደገለጹት ኢህዓዴግ ሀገሪቱን ሲቆጣጠር…

Continue reading

በጉራጌ ዞን በአበሽጌ ወረዳ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ከ 6 መቶ በላይ ምልምል ህዝባዊ ሰራዊት አባላት በዛሬው እለት ተመረቁ ፡፡

ምልምል ህዝባዊ ሰራዊቱ የአካባቢያቸው ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ለሀገሪቱ ደጀን በመሆናቸው አደረጃጀቶችን አጠናከረው በልማት ስራው ጭምር በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡ የምርቃት ዝግጅቱ ላይ ተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንዳሉት…

Continue reading

በመሰረታዊ ውትድርና ያሠለጠናቸው ከ8መቶ በላይ የህዝባዊ የሰራዊት አባላት በዛሬው እለት ማስመረቁን የእዣ ወረዳ አስተዳደር ገለፀ።

ተመራቂዎች የአካባቢያቸውን ሰላም ከመጠበቅ ባሻገር ሀገራችን የጀመረችውን የህልውና ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን መስዋአትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የእዣ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት ተመራቂ ህዝባዊ ሰራዊት አባላት በንድፈ…

Continue reading

ህዳር 26/2014 የአመጋገብ ስርዓት በማሻሻል ጤናማ አምራችና ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።

ሀንገር ፕሮጀክት በስርዓተ ምግብ አተገባበር ላይ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዎርክ ሾፕ አዘጋጀ። የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ የስርዓተ ምግብ ተግባር የአንድ ተቋም ተግባር…

Continue reading

ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚዉል የበሶ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በከተማዉ ለ5ኛ ዙር በግንባር እየተዋደቀ ላለዉ የሰራዊት አባላት በሶ አሽጎ ለመላክ እየሰሩ እንደሆነም አንዳንድ የከተማው ሴቶች አስታዉቀል። የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሄኖክ አብድልሰመድ እንደገለፁት የከተማዉ ህዝብና መንግስት…

Continue reading

ሀገራችን ከስንዴ ልመና ለመታደግ በበጋ መስኖ ስንዴ የማልማቱ ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የበጋ መስኖ ስንዴ ዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም ከክልል፣ከዞንና ከወረዳ የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዞኑ በጉመር ወረዳ በአበሱጃ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት…

Continue reading