የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም አፈጻጸም ዙሪያ ከሳውዲ አረቢያ የዋሽ ፕሮግራም ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም አፈጻጸም ዙሪያ ከሳውዲ አረቢያ የዋሽ ፕሮግራም ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም ከሳውዲ አረቢ የዋሽ ፕሮግራም ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለተኛው ፌዝ የዋሽ ፕሮግራምን አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ለአጋር ድርጅቱ ተወካዮች አብራርተዋል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ሉሌ በበኩላቸውፕሮግራሙ በ7 አጋር አካላት ማለትም እንግሊዝ ኤምባሲ፣ አለም ባንክ፣ ዩኒሴፍ፣ የፊንላንድ መንግስት፣ ኔዘርላድ መንግስት እና የሳውዲ መንግስት የሚደገፍ ሲሆን፤ ከሳውዲ መንግስት የዋን ዋሽ ተወካዮች ጋር በውሃና ኢነርጂና በፋይናንስ ሚነስቴር እየተተገበሩ ያሉትን የከተማና ገጠር ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ምን ላይ እንደደረሱ እና ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አቶ ተስፋዩ በማያያዝ ዋን ዋሽ ፕሮግራም በአገራችን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ እና ከ1.5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው፤ ለተወካዮችም በውሃና ኢነርጂ በኩል ፊዚካል ስራዎችን በገንዘብ ሚኒስትር የፋይናንስን ፕሮግራሞች አፈጻጸምን አስመልቶ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡

የሳውዲ ተወካዮችም በበኩላቸው በስራ አፈጻጸሙ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ለዚህም ማሳያ በቀጣይ ፌዝ ሶስት ላይ የተሻለ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
መረጃው የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።

መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *