የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወልቂጤ ማዕከል 3ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ሰልጣኝ አመራሮች በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ሰነንና ቆረፍቻ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማው የገብስ ማሳ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።


የብልጽግና ፓርቲ ሶስተኛ ዙር የአመራሮች “የህልም ጉልበት እምርታዊ እድገት” ስልጠና በወልቂጤ ማዕከል እየወሰዱ ይገኛሉ።

በወረዳው በሰነንና ቆረፍቻ ቀበሌ 3መቶ 88 ወጣቶች፣ አርሶ አደሮችና ሴቶች በ103 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ያለሙት የገብስ ማሳ የመስክ ምልከታ እያደረጉ ነው።

ስልጠናው ሰልጣኝ አመራሮች በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ሀገራዊ ፣ቀጠናዊ፣አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያለመ ነው።

ሰልጣኝ አመራሮችም በመስክ ምልከታው ያዩትን ምርጥ ተሞክሮ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች በማስፋት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይኖርባቸዋል።

በመስክ ምልከታው የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣ የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ፣ የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን እና የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ ሰልጣኝ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *