ስልጠናው ሰልጣኝ አመራሮች በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ሀገራዊ ፣ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያለመ ነው።

በዚህም ሰልጣኞች በንድፈሀሳብ የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ለማዋሀድና ለመመልከት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ በጉራ ወልቂጤ ከተማ የለሙ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የጤፍ እና የበቆሎ ማሳዎች እንዲሁም ፋብሪካዎች እየጎበኙ ሲሆን እንደ ሀገር ለተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ማሳለጥ የሚያስችል ስራዎችን ሰልጣኞቹ ምልከታ አድርገዋል።

ይህም በአመራሩ ዘንድ የልምድ ልውውጥ መከናወኑ በየአካባቢው ተመሳሳይ ልማትን ለማምጣት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑም አመራሮቹ ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *