በጉራጌ ዞን እኖር እና እኖር ኤነር መገር ወረዳዎች የተለያዩ የወባ በሽታ ወረርሽን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
በየመዋቅሮቹ የተጀመሩ የወባ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፣ በመከላከሉ ላይ የማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚያጠናክሩ ተግባራት በተለይም ለወባ ትንኝ መራቢያ አከባቢዎችን በማፋሰስና በማዳፈን የአካባቢ ቁጥጥር በመስራት፣ የቤት ለቤት አጎበርን በአግባቡ እንዲጠቀም ግንዛቤ መፍጠር ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው።
የቤት ለቤት ጉብኝት በማድረግ የታመሙ ሰዎችን በመለየት ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ የማድረግ ስራ፣ የወባ ህክምናና ምርመራ ስርዓቱን በጤና ጣቢያና በጤና ኬላ ማጠናከር፣ በወረዳ እና በጤና ጣቢያ የሚገኙ የመድሃኒት እና የላብራቶሪ ግብዓት ወደ የጤና ኬላዎች እንዲደርስ ማድረግ፣ በት/ቤቶች እና በሀይማኖት ተቋማት የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት፣ በጤና ጣቢያ፣ በወረዳ ጤና ጽ/ቤት፣ በወረዳ አስተዳደር ደረጃ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን (RRT) በተቀመጠለት ጊዜ አፈፃፀም ግምገማ ማድረግ እንደሚገባ ከወረዳ አስተዳዳሮዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በቀበሌና በጤና ጣቢያ በታዩት ላይ በሁለቱም ወረዳዎች ለወረዳ አስተዳዳር እና ለሚመለከታቸው አካላት ገብረ መልስ ተሰጥቷል።
መረጃው የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ነው