አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ምርትና ምርታማነትን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ግብዓትን በማቅረብ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በ157 መሰረታዊ ህብረት ስራዎች የተቋቋመ ዩኒየን ነው፡፡
ዩኒየኑ ከግብዓት አቅርቦት በተጨማሪ በ2010 ዓ.ም በተወሰነው የትርፍ ክፍፍል መሰረት ለአባል መሰረታዊ ህብረት ስራዎች ለማከፋፈል በትኩረት የሚሰራ ሲሆን ትርፋማነቱን በማሳደግ አባላቱ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ አመርጋ ገልፀዋል፡፡
ዩኒየኑ አርሶ አደሩ ምርት በሚሰበስብበት ወቅት ምርቱ በተገቢው ዋጋ እየገዛ ለሸማቾች በተመጣጣ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
እንደ አቶ አበበ ገለፃ ዩኒየኑ የተቋቋመበት ዓላማ እንዲሳካ ሰራተኞቹ ተግባሮቻቸው እቅድን መሰረት በማድረግ እንዲያከናውኑና የተደራጀ ሪፖርት ማዘጋጀት እንዲችሉ ያለመ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ስልጠናው ከእቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ባለፈ እቅዳቸውን መሰረት በማድረግ የሚሰጣቸው ግብረ መልስ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው በመሆኑ በአጭር ቀናት ውስጥ ዩኒየኑ ጥራት ያለው ዩኒየኑን ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል እቅድ እንደሚዘጋጅ አቶ አበበ ገልጸዋል፡፡
የዩኒየኑ የበጀት ዓመት የሚጠናቀቀው መስከረም 30 በመሆኑ ሰራተኞቹ ጥራት ያለው፣ የሚተነተንና ዩኒየኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል የዩኒየኑ፣ የስራ ክፍሎችና የፈፃሚዎች የ2017 በጀት ዓመት ከጥቅምት እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም በስልጠናው ባገኙት ክህሎት መሰረት ከማቀድ ጎን ለጎን ለትግበራው ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
አክለውም አቶ አበበ አባላቱ ስለ ዩኒየኑ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖረው ትክክለኛ መረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት የሚሰራ ሲሆን ዩኒየኑ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት ከአባላቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ ዩኒየኑ ምርትና ምርታማነትን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ማቅረብ እንዲችል ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ከተሳተፉ የዩኒየኑ ሰራተኞች መካከል ወ/ሮ ዚያዳ አብደላ እና አቶ አዲሱ አስናቀ ተጠቃሽ ሲሆኑ ተግባራት ያለ እቅድ ማከናወን የባለሞያዎች አቅም እና የተቋሙ ትርፋማነት ያለበትን ደረጃ እንዳይታወቅ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ስለ እቅድ እና ሪፖርት አዘገጃጀት የነበራቸው ግንዛቤ አነስተኛ እንደነበር የተናገሩት ሰልጣኞቹ በእቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመለወጥ የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
Your writing is like a breath of fresh air in the often stale world of online content. Your unique perspective and engaging style set you apart from the crowd. Thank you for sharing your talents with us.
Download music private server, MP3/FLAC/Clips/Labels https://0daymusic.org/ all access 440 TB music scene realeses.
Download music private server, MP3/FLAC/Clips/Labels https://0daymusic.org/ all access 440 TB music scene realeses.