የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ “ሰላም በእጄ፣ ብልጽግና በደጄ፣ የመደመር ትውልድ ሚና” በሚል የወጣቶች ሊግ አባላትና ለተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ዞናዊ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ወጣቶች በሀገሪቱ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሀገር ለወጥ እንዲመጣና እንዲጸና እያደረጉት ያለው ጥረት አጠናክረው ማስቀጠል ይኖርባቸዋል።
ከነጠላ ትርክት አስተሳሰብ በመውጣት ገዢ ትርክት ላይ ማትኮር ይገባል ያሉት አቶ ላጫ በዞኑ የሀይማኖት ጽንፈኝነትና አክራሪነት በመቃወም ከዚህ ቀደም የነበረውን ተከባብሮ የመኖር ዕሴት ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዞኑ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በግብርና ዘርፍ በመሰማራት አስደናቂ ስራ እየሰሩ ያለው ስራ በቀጣይም ማስቀጠል ይኖርችኃል ነው ያሉት።
ህገወጥነት፣ ሌብነት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር መጸየፍና መታገል ከወጣቱ እንደሚጠበቅ ገልጸው በዚህም በየአካባቢው ያሉ የወል መሬት ላይ ያለው ህገወጥነት መከላከል ይኖርባችኋል ብለዋል።
የጉራጌ ብሔረሰብ አስደናቂ ባህል እንዳለው ገልጸው ባህሉና ቋንቋው ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ወጣቱ ትውልድም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።
በዞኑ የሀዋሪያት ከተማ የግብአት ችግር ለመፍታት፣ የከሬብ መስኖ፣ ሀዋሪያት ማዞሪያ እስከ ሀዋሪያት ያለው መንገድ ወደ አስፋልት ለመቀየር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል በበኩላቸው ወጣቱ ከአመራሩ ጎን በመቆም በዞኑ ሰላምና ልማት ይበልጥ እንዲረጋገጥ በመስራት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።
የዞኑ ወጣቶች ለውጡ እንዲመጣ የከፈሉት ዋጋ ከፍተኛ መሆኑ ገልጸው ይህ ለውጥ ይበልጥ እንዲጸና በትኩረት እንዲሰሩም ተናግረዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ በስራ ታታሪነቱና ወዳድነቱ የሚታወቅ መሆኑን ያነሱት አቶ አለማየሁ ወጣቶች ጊዜያቸውን በሱስና አሉባሌ ቦታ ከመዋል ይልቅ የቀድሞ የአባቶቹን የስራ ታታሪነት በማስቀጠል በተለያዩ መስኮች በመሰማራት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ወጣቱ ትውልድ ለሰላምና ለልማት ቅድሚያ በመስጠት መስራት እንዳለባቸው አንስተው በዞኑ ያሉ ጸጋዎችን በተገቢው በመጠቀም ይበልጥ መስራት ይገባል ብለዋል።
በፌደራል ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰንበቶ አባቡ እንዳሉት እንደ ሀገር የመጣውን ለውጥ ይበልጥ በማጽናት በልማት ስራ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል።
ወጣቶች ቴክኖሎጂ ለበጎ አላማ በማዋል ለሀገር ግንባታና ለህዝቦች ተጠቃሚነት መጠቀም ይኖርባችኋል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ሰፊ ቅባቱ ወጣቶች የጋራ ትርክት በማስፋትና ሰላም በማፅናት በፖርቲው የወረዱ ኢንሼቲቮች በግንባር ቀደምትነት በመተግበር የተጀመረውን የሀገር ግንባታ ሂደት ዋንኛው ተዋናይ መሆን እንዳለባቸው አመላክተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ ከዚህ ቀደም የነበሩ የሰላምና ጸጥታ ችግሮችን በመፍታት በሰላምና በልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው በቀጣይም ወጣቱ በሰላምና በልማት ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ አንስተዋል።
ወጣቱ በተለያዩ የስራ መስክ ላይ ተሰማርቶ ለመስራት የመብራት ችግር እንዲፈታና ለወጣቱ የስራ ዕድል መፍጠርና ብድር ማመቻቸት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል።
የወልቂጤ ከተማ የማስተር ፕላን፣ የከሬብ መስኖ፣ የሀዋሪያት ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግብአት ችግር፣ ከአገና ማዞሪያ ምሁር አክሊል ወረዳ ያለው መንገድ አስፓልት እንዲሆን፣ ለወጣቶች የቴክኖሎጂ በተለይም የትራክርት አቅርቦት ብሎም የስብዕና ማዕከል ግንባታ፣ በዞኑ ትላልቅ ፋብሪካዎች እንዲገነቡ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ወጣቶቹ ጠይቀዋል።