የህዝብና የመንግስትን አቅም በማስተባበር በወረዳዉ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የአበሽጌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።
በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አስተዳደር በወረዳዉ እየተሰሩ ባሉ የልማት ስራዎች ዙሪያ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ዉይይት ተደርጓል።
የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር እንዳሉት በወረዳዉ የማህበረሰቡና የመንግስት አቅም በማስተባበር በተለያዩ የልማት ዘርፎች አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል።
የተጀመሩ የልማት ሰራዎች ስኬታማ ለማድረግ ቅንጅታዊዉ ስራ የበለጠ በማጠናከር የሚፈለገዉ ዉጤት ማምጣት ይገባልም ብለዋል።
ወረዳዉ በግብርናዉ ዘርፍ ትልቅ ፖቴንሻል እንዳለም ያመላከቱት አቶ ካሱ ዘርና ማዳበሪያ በፍትሃዊነት ለአርሶአደሩ ተደራሽ ለማድረግ ከዞኑ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዉ በዚህም የሚፈለገዉ ዉጤት ማምጣት መቻሉም ተናግረዋል።
በሁሉም አካባቢዎች ላይ የመንግስት ኢንሼቲቭ የሆኑ ስራዎች በተለይ 30 ፣ 40፣ 30ና ሁሉም ነገር በአቀፈ መልኩ በወረዳዉ ዉጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆነም አስረድተዋል።
ከቀበሌ ጀምሮ በማህበረሰቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የህዝቡን አቅም በተገቢዉ በመጠቀም ረገድ አመራሩ በቅንጅት መስራት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በመንገድ ፣በንጹሁ መጠጥ ዉሃ ግንባታ እንዲሁም በሌሎች የልማት ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚበረታታ እንደሆነም ተናግረዉ ጀጀባ ላይ ከፍተኛ ብር የወጣበት የመንገድ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ፣ ከወልቂጤ ቱባ የመንገድ ግንባታ አልቆለት በቅርቡ የሚመረቁም እንደሆነም ተናግረዋል።
ከነዚህም በተጨማሪ በቦረር ቀበሌ ባለሀብትና የቀበሌዉ ማህበረሰብ በማስተባበር ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ደረጃዉን የጠበቀ ጠጠር መንገድ መገንባት የተቻለና ሌሎችም በርካታ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በወረዳዉ በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አመላክተዉ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ በሁሉም ቀበሌዎች አንድ አዲስ ቤት ግንባታና አንድ የጥገና ስራ እየተሰራም እንደሆነም ተናግረዋል።
የአበሽጌ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ፈቀደ እንዳሉት መድረኩ በዋናነት በወረዳዉ የተሰሩ የልማት ስራዎች እዉቅና መስጠት ይገባል ብለዉ በሁሉም ቀበሌዎች እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆነም ተናግረዋል።
የህዝባችን የመልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት መስራት ይገባልም ብለዋል።
ሀገር ወደ ምትፈልግዉ የብልጽግና ማማ ላይ ለመድረስ ቁጠባ ወሳኝ እንደሆነም ያመላከቱት አቶ ሙሉጌታ ለዛሬዉ መድረክ አጋዥ የሆነዉን የዳሽን ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይገባልም ብለዋል።
የዳሽን ባንክ የጅማ ዲስትሪክት የወለድ ነጻ አገልግሎት ተጠሪ አቶ መሀመድ አደም በዉይይት መድረኩ ተገኝተዉ እንዳሉት ባንኩ ባለፉት 30 ዓመታት በሀገሪቱ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ጉልህ አስተዋጾኦ እያደረገ ይገኛል።
ባንኩ በዞኑ 6 ቅርንጫፎች 1 ንኡስ ቅርንጫፍ በመክፈት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶች ለደንበኞች እየሰጠ እንደሆነም አመላክተዉ የተለያዩ ሀላፊነት ማህበራዊ ሀላፊነት ከመወጣት አንጻር ባለፈዉ አመት እና በዘንድሮ የመስቀል በአል በጉራጌ ባዛርና ኤግዚቢሽን አጋር በመሆን ዝግጅቱን የተሳካ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱም አስታዉሰዉ ባንኩ የወረዳዉ እድገት ከመደገፍ አንጻር የበኩሉን እንደሚያደርግም አመላክተዋል።
በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ቅንጅታዊ አሰራሩን በማጠናከር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ከቀበሌ አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በልማትና መልካም አስተዳደር የሚስተዋሉ ዉስንነቶች በተገቢዉ በመቅረፍ ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።
የአካባቢዉ ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ረገድ የሁሉም ሰዉ ሀላፊነት እንደሆነም አመላክተዉ በዚህ ዘርፍ የበለጠ ተቀናጅቶ ሊሰራበት ይገባልም ብለዉ ጸረ ሰላም ሀይሎች ለህግ አሳልፎ መስጠት ይገባል ብለዋል።
ከበጎ ፍቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታና እየተደረጉ ያሉ ሌሎችም ድጋፎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በመድረኩም በወረዳዉ በአንዳንድ አካባቢዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች በዶክመንተሪ ፊልም ቀርቦ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።