የጉራጌ ባህላዊ እሴቶች በማጥናት ፣ዶክመንት በማድረግና ለትውልድ እንዲተላለፉ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንደሚወጣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።

የይህ የተባለው የጉራጌ ዞን 7ኛው የመስቀል ፌስቲቫል በእኖር ወረዳ በጋህራድ ጀፎሮረ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በተከበረበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የቅርስ ተመራማሪ ዳይሬክተር ዶ/ር ታደሰ ሰለሞን ፌስቲቫሉ የተጀመሩ የጥናት ስራዎች ትልቅ ግብአት ለማግኘት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

አክለውም እንደ ሀገር ያሉንን እሴቶች እንድናውቅ ፣የጉራጌ ድንቅ ጥበብና ሀብት እንድንረዳ ፣የጥናት ስራዎችም መጠናከር እንዳለባቸው የሚያመላክት እና ብዙ መገለጫዎች ያሉት መሆኑን ዶ/ር ታደሰ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለማነቃቃት ባህልና እሴቱ ይበልጥ እንዲጠብቀው እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላል ብለዋል።

ባለስልጣኑም ከዞኑ ጋር ያለው ቅንጅት በማጠናከር የጉራጌ ባህላዊ እሴቶች በማጥናት ፣ዶክመንት የማድረግና ለትውልድ እንዲተላለፉ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ በበኩላቸው በዓሉ ለ300 አመታት በላይ ተደብቆ የነበረው ቅዱስ መስቀል በንግስት እሌኒ የተገኘበት ሁኔታ በማሰብ የሚዘከር በመሆኑ በደስታ የሚከበር በአል መሆኑን ተናግረዋል።

ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር የጉራጌ ብሔር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጥ በአል መሆኑን አውስተዋል።

የጋብቻ ስርዓት የሚፈፀምበት የተጣላ የሚታረቅበት የተቸገረ ሚረዳበት የተራራቁ የሚገናኙበት እንስሳትም ጭምር የሚቦርቁበት መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ መብራቴ አክለውም ስለ ሰላም ፣ አንድነት ፣ አብሮነትና ልማት የሚመካከሩበት እንደሆነም በፌስቲቫሉ ተናግረዋል።

በእለቱም የጉራጌ የባህላዊ ምግብ አውደ እርይ እና የመስቀል የምግብ አዘገጃጀት ፣ የደመራ ስነ ስርአት ጨምሮ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች በፌስቲቫሉ ተከናውነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *