በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በመኸር እርሻ 4 ሺህ 1 መቶ 133 ሄ/ር መሬት ሰብል መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ ሳህሌ በቅኝት ወቅት እንደገለጹት አርሶ አደሮች የባለሙያዎች ምክረሀሳብ ተግባራዊ ማድረግ በመቻላቸው በዘንድሮ የመኸር ወቅት የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ መላኩ በወረዳው የተለያዩ አካባቢዎች ተዛውረው በማለት በዚህም ወቅት የመኸር ሰብል ቁመና የአርሶ አደሩ የአረም ቁጥጥርና የማሳ እንክብካቤ ተጠናክሮ እንደቀጠለም ገልፀዋል።

የአርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በዘንድሮው ደረጃ በጤፍ፣ በስንዴ፣ በገብስ፣በአተር ፣ የባቄላ፣በበቆሎና በሌሎች ሰብሎች በኩታገጠም እንዲለሙ መደረጉን የገለጹት ኃላፊው በወረዳው እየለማ የሚገኘው የመኸር ሰብል አሁናዊ ቁመና እጅግ አስደሳችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት፣ የመካናይዜሽንና አማራጭ የመስኖ ልማት ስራዎች አለመስፋፋት በአርሶ አደሮቹ ተጠቃሚነት ላይ ተፅዕኖ ቢኖራቸውም የአርሶ አደሮች ክህሎት እያደገ በመምጣቱ በምርትና ምርታማነት እድገት ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አበረታች መሆኑን አቶ መላኩ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ጊዜዉ የአረም ቁጥጥር በማድረግና የስንዴ በሽታ የመከላከል ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል በማለት በተጨማሪም የአመራሩና የባለሙያው ድጋፍ አሰጣጥና ክትትል ሂደት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል።
ዘገባው የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *