በእኖር ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የፓርቲና የመንግስት የልማት እንቅስቃሴዎች ምርጥ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልና የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሱፐርቪዥን ልዑካን ቡድን በእኖር ወረዳ ሲያደርግ የነበረውን የሱፐርቪዥን ስራ መጠናቀቁን የእኖር ወረዳ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የሱፐርቪዥን ቡድኑም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ በወ/ሮ ሰርካለም ሳሙኤል፣የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና የፓርቲ ጽ/ቤት ተወካይ በአቶ ሄኖክ አ/ሰመድ እንደሁም የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምርያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ በሆኑት አቶ አደም ሽኩር ሱፐርቪዥን የተመራ ነበር።

የድጋፋዊ ክትትል ቡድን መሪዎች በጋራ እንደገለፁት የሱፐርቪዥኑ ዋና አላማ በወረዳው የተረጂነት እርሻ እና በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት ያለበት ደረጃ ለመመልከት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በየምዕራፉ የሚገኙ ተግባራት፣የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና ሰው ተኮር የመልካም አስተዳደር ስራዎች ያሉበት ደረጃ ለመፈተሽና ሞዴል መሆን የሚችሉ አደረጃጀቶችና ቀበሌዎችን በመለየት ለሌሎች ምርጥ ተሞክሮ የሆኑትን ለመያዝ እንደሆነም አመላክተዋል።

በምልከታውም በወረዳው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተስፋ ሰጪ ጉዞ ዕዉን ለማድረግ ዳአምር ቀበሌ በሚገኘው የወል መሬት 25 ሄ/ር የሚሆን የጤፍ ማሳ፣ጠረደ ቀበሌ በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰሩ ቤቶች እንደሁም ካሳይ ቀበሌ አሁን በመገንባት ላይ የሚገኘው አቅመ ደካማና ማየት የተሳናቸው የወ/ሮ ለይላ ሁሴን ቤት ተዟዙረው ተመልክተዋል።

ወረዳው እየሰራቸው ያሉ የልማትና የፓርቲ እንቅስቃሴዎች ከዞንና ከክልል አልፎ ለሀገርም ምርጥ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ያነሱት የሱፐርቪዥን ቡድን መሪዎቹ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን አቀናጅቶ ከመስራት አኳያ ያለውን ጥንካሬ በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞሸዲን አህመድ በድጋፍ ክትትሉ ወቅት እንዳሉት በመንግስትና በፓርቲ የታቀዱ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ያሉንን አቅሞች አሟጠን በመጠቀም ወረዳው በሁሉም ዘርፎች ሞዴል ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተከናውኗል ብለዋል።

እንደ አቶ ሞሸዲን አህመድ ገለፃ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በወረዳችን እየተሰሩ ያሉ የግብርና ስራዎች፣የበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣የኑሮ ውድነት በመቀነስና ገበያን በማረጋጋት፣በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ ስራዎችና በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በድጋፍና ክትትሉ ማጠቃለያ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመፈተሽ የሱፐርቪዥን ቡድን መሪዎቹ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

በድጋፍ ክትትሉና በመስክ ምልከታው የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ ጨምሮ የፓርቲ አመራሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መረጃው የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *