ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ የግብ ስምምነት ላይ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የልማት ስራዎች ለህዝቡ በማቅረብ ይበልጥ የልማቱ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት ይገባል።

በመሆኑም በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ይበልጥ ለማሳለጥ የኮሚኒኬሽንና የሚዲያ ዘርፉን ይበልጥ መደገፍ እንደሚገባ አቶ አበራ ተናግሯል።

የሚሰሩ ስራዎች በሚዲያ በማውጣቱ እረገድ ሁሉም መዋቅሮች መረጃዎችን እርስ በርስ በመጋራት በሁሉም ቦታ ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ አበራ አክለውም ለብዙ ጊዜ ሲጠየቅ የነበረው የጉራጌ የማህበረሰብ የቴሌቬዥን ጣበያ ለማቋቋም ዞኑ መነሻ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን እደገለፁት ጉራጌ የሚነገርለት፣የሚጻፍለት እና የሚተዋወቁለት በርካታ ጉዳዮች ያሉት ትልቅ ማህበረሰብ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ይህንን ማህበረሰብ የሚመጥን የሚዲያ ስራ ለመስራት ያሉንን የሚዲያ አማራጮች በማብዛት እና ተደራሽነትን በማስፋት የህብረተሰባችን የመረጃ ፍላጎት ማርካት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

በሬድዮ ፣በቴሌቭዥን ፣በማህበራዊ ሚዲያዎች ፣በህትመት እና በገጽ ለገጽ የሚዲያ አማራጮች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

አቶ ሀዲሞ አክለውም ማህበረሰቡን የሚመጥን እና ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ በመጠቆም።

ተቋሙን ማገዝ ማለት የሌሎች ተቋማት ስራዎች ማገዝ መሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ሀዲሞ ዘመኑን የዋጀ የኮሚኒኬሽን ተቋም ለመገንባት በቁሳቁስ በሰው ሀይል፣በበጀት እና የክህሎት ስልጠናዎች ማመመቻቸት እና በሌሎችም መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንዳሉት የሚዲያ ቁሳቁስ ፣ የቢሮ፣የበጀት ፣የሰው ሀይል እና ሌሎችም አለመሟላት በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት እንዳይመጣ አድርጎታል ብለዋል።

አያይዘውም ጉራጌ የራሱ የሆነ የማህበረሰብ የቴሌቪዥን ጣበያ ባለመኖሩ መረጃን በሚፈለገው ጊዜና ፍላጎት ማድረስ እየተቻለ ባለመሆኑ የራሱ ሚዲያ ሊኖረው እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በዞኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው ያሉት ሀሳብ ሰጪዎቹ የወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬድዮ የስርጭት አድማሱን በማስፋት ለህብረተሰቡ መረጃ በወቅቱ የማድረስ ተግባሩ ማጠናከር እንዳለበት አንስተዋል።

ለባለሙያው ስልጠናዎችን በመስጠት ፣ሁሉም የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ወቅቱን የሚመጥን መረጃ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በእለቱም መምሪያው ከወረዳዎች ጋር የ2017 እቅድ የግብ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ከ1 እስከ 3 የወጡ መዋቅሮች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። በዚህ መሰረት፦
1ኛ ጉመር ወረዳ
2ኛ እኖር ወረዳ
3ኛ እዣ ወረዳ ሲሆኑ ከከተማ አስተዳደሮች ደግሞ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *