የንግዱ ማህበረሰብ ዶላር ጨምሯል በሚል በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ጭማሪና ምርት የሚደብቁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑም የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ በወልቂጤ ከተማ የዋጋ ማረጋጋያ ከተቋቋመዉ ግብረ ሀይል ጋር የተሰሩ ስራዎች ላይ በዛሬ እለት ወልቂጤ ከተማ ተወያይተዋል።

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ እንዳሉት መንግስት የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ ያለ አግባብ ዋጋ የሚጨምሩና ምርት የሚደብቁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ይገኛል።

በሁሉም መዋቀሮች ግብረሀይል ተዋቅሮ ማሻሻያዉን ተከትሎ ህገወጥነት እንዳይኖር ለሸማቹ ፣ለነጋዴዉ ፣ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለሚዲያ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዞኑ 100 የእህል መጋዘኖች ፣120 የኮንስትራክሽን እቃዎች መሸጫ ሱቆች ፣ 40 ዳቦ ቤቶች ፣20 ጅምላ አከፋፋዮች ፣ 150 የችርቻሮ ሱቆች ክትትል የተደረገባቸዉ ሲሆን ከነዚህም 39 ድርጅቶች ላይ ጉድለት የተገኘባቸዉ መሆኑንና 36ቱ ድርጅቶች የማሸግና የ10 ድርጅቶች ባለቤቶች በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ መሰራቱም ጠቁመዋል።

25 ድርጅቶች የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እና ከነዚህም በአስተዳደራዊ ቅጣት 141 ሺ ብር የተገኘ እንደሆነ አመላክተዉ 11 ድርጅቶች በሂደት ላይ መሆናቸዉም ጠቅሰዋል።

በተደረገዉ የክትትልና የቁጥጥር ስራ በምርቶች ላይ አላስፈላጊ ዋጋ ጭማሪ እና ምርት ማሸሽና መደበቅ መቀነሱና ነጋዴዎች ህጋዊ መስመር እንዲይዙ ተደርጓል ብለዉ በዘርፉ የሚጠበቀዉ ዉጤት እንዲመጣ ማህበረሰቡ በህገ ወጦች ላይ እየሰጠዉ ያለዉን ጥቆማ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በዞኑ በ15ቱም መዋቀሮች ለ68 ሺህ 5 መቶ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራቱም አብራርተዉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዉ በቅንጅት ተሰርታል፡፡

በወልቂጤ ከተማ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ህግ በማስከበር ረገድ እየተሰራ ያለዉን ስራ የሚበረታታና በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንዳሉት ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በከተማዉ ዋጋ በጨመሩና ምርት በደበቁ 25 የንግድ ተቋማት የማሸግ ስራ መሰራቱም ጠቁመዋል።

በተለያዩ ዘዴዎች ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ እየተፈጠረ ይገኛል ብለዉ እንደ ከተማ የተዋቀረው አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ ተግባሩ እየገመገመና እየተከታተለ እንደሆነም ተናጎሯል።

አሁንም ህዝብ በሚያማርሩ ነጋዴዎች ላይ ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሀላፊዉ ማህበረሰቡ የተለመደው ጥቆማ ለተቋሙ ብሎም ለክልል መዋቅር በነፃ ስልክ 9348 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪም አቅርበዋል።

በዉይይት መድረኩ የተገኙ የወልቂጤ ከተማ የዋጋ ማረጋጋያ ከተቋቋመዉ የግብረ ሀይሎች አንዳንድ አባላት በሰጡት አስተያየት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪና ምርት የሚሸሽጉ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸዉ እንደሆነና ይህንንም አጠናክረዉ እንደሚሰሩበትም አብራርተዋል።

በከተማዉ ዉስጥ በቆርቆሮ ፣በሲሚንቶ ፣በዘይትና በሌሎችም ምርቶች ጭማሪ የሚስተዋል ሲሆን እነዚህ አካላቶች አሁንም ከድሪጊታቸዉ ሊታቀቡ እንደሚገባና ካልታቀቡ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ አብራርተዉ ማህበረሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የሰንበት ገበያዉን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *