ከመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ስራ አስፈጻሚዎች በጉራጌ ዞን እምድብርና ቸሃ ወረዳ የልምድ ልውውጥ አካሂዳል።

ከመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ስራ አስፈጻሚዎች በጉራጌ ዞን እምድብርና ቸሃ ወረዳ የልምድ ልውውጥ አካሂዳል።

የኢፌድሪ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ወይዘሪት አባንግ ኩሙዳን እንዳሉት የልምድ ልውውጡ አላማ በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ በወጣቶች በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች በማስፋት ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የወጣቶች ሊግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለ በቀለ በዞኑ በወጣቶች በግብርና በሁሉም መስክ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች ናቸው።

ወጣቶች ከስራ አጥነት አመለካከት በመውጣት ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ለማድረግ መስራት ይገባል ያሉት ኃላፊዋ በዞኑ ወጣቶች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ ዕድል በመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራ አድንቀዋል።

በተለይም ባህርዛፍን በማንሳት በቦታው የተለያዩ አዝዕርት ሰብሎችን በማልማት ለሌሎች ሀብት መፍጠርና ማስተዳደር እንደሚቻል ያሳየ ተግባር በመሆኑ በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ ወጣቶችም ያገኙትን ልምድ ወስደው በአካባቢያቸው ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር በበኩላቸው እንደ ሀገር የወረደው የሌማት ትሩፋት እንሼቲቭ ላይ በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ ተጠቃሚነታቸው ይበልጥ እንዲረጋጋጥ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ሁሉንም የልማት አቅሞች በብልሃትና በትጋት በማልማት የምግብ ዋስት ከማረጋገጥ ባለፈ ድህነትን ለማሸነፍ የወጣቶችን እምቅ አቅም በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል ፡፡

በዞኑ እምድብር ከተማ በወጣቶች እየተከናወኑ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሁሉም የክልልና የሀገሪቱ ወጣቶች በማስፋት እና እንደ ሀገር እየተደረገ ባለው ሁሉ አቀፍ ብልጽግናን የማረጋገጥ ሂደት የወጣቶች ሚና አሁን ካለው ይበልጥ እንዲጠናከር ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ እንዳሉት ወጣቶች በሁሉም ዘርፍ ተሳትፎአቸው እንዲጎለብት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ከልማት ስራ ጎን ለጎን በሰላምና በወጣቱ ስብዕና ግንባታ ዘርፍ በትኩረት በመስራት ዞናዊ ለውጥ ለማጠናከር በየአደረጃጀታቸው ይበልጥ አጠናክሮ መስራት ይገባል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው በዞኑ በሌማት ትሩፋት በከተማና በወረዳ በወተት 304፣ በዶሮ 504፣ በማር 150፣ የስጋ ከ81ና የአሳ ከ10 በላይ መንደሮችን መፍጠር ተችላል።

በዚህም በዘርፉ በሁሉም መስኮች በትኩረት በመሰራቱ ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የአርሶ አደሩ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እየተቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በከተማና በገጠር በትንሽ ቦታ ብዙ ምርት ማምረት እንደሚቻልና ባህርዛፍ በማንሳት ስፍራው በፍራፍሬ በመተካት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት መስራት እንደሚገባ ገልጸው በዞኑ ያሉ ጸጋዎችን በተገቢው አቀናጅቶ በመጠቀም የአርሶ አደሩና የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ነው ያሉት።

ወጣት አብድልሰላም አብድልጀሊል ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ወጣት ጋትቤል ፖክ ከጋምቤላ ክልል በልምድ ልውውጡ ከተሳተፉት መካከል ይገኙበታል።

ወጣቶቹ እንዳሉት በዞኑ የብልጽግና እሳቤ ተከትሎ ወጣቶች በግብርናው ዘርፍ እየሰሩት ያለው ስራ አድንቀው ያዩት ምርጥ ተሞክሮም ወደ ክልላቸው በመውሰድ አስፍተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በእምድብር ከተማ አስተዳደር በዶሮ፣ በከተማ ግብርና፣ በወተት ልማት የተሰማሩ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት በትንሽ ቦታ በማምረት ከራሳቸው አልፈው ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቶች ከስራ ጠባቂነት በመውጣት ስራ በመፍጠር መስራት እንዳለባቸው መክረዋል።

በእለቱም የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ አንዲት አቅመ ደካማ ቤት አፍርሶ በአዲስ የመገንባት፣ የችግኝ ተከላ፣ በወጣቶች እየተሰሩ ያሉ የወተት፣ የዶሮ፣ የሙዝ ብሎም በከተማና በገጠር እየለሙ ያሉ የፍራፍሬ ስራዎችን ጉብኝት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *