በሀገሪቱ ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ህብረተሰቡ በትምህርት ስራ ላይ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ፡፡

በሀገሪቱ ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ህብረተሰቡ በትምህርት ስራ ላይ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ፡፡

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የቆጠር ገድራ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡

በትምህርት ቤቱ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ግንባታና ነባር የመማሪ ክፍሎች እድሳት በማጠናቀቅ ተመርቆ ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ- ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት ትምህርት የአዓለም ስርዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በመሆኑም የህብረተሰቡ እድገት መሻሻል፣ የተሟላ ስብዕና ያላቸው ዜጎች ለመፍጠር፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት ለማስመዝገብና የሰለጠነ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም በሀገሪቱ ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የሚያስችሉ የትምህርት ግብዓትና መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እየተከናወነ እንደሚገኝ ክብርት አፈ ጉባኤዋ ገልጸዋል፡፡

በሀገሪቱ ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በአይነቱ ልዩ የሆነ ትምህርት ለትውልድ በሚል የተዘጋጀው የንቅናቄ ስራ ህብረተሰቡ በማሳተፍ በግንባር ቀደምትነት ከፈጸሙ የክልሉ አካባቢዎች አንዱ የጉራጌ ዞን መሆኑን ክብርት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገልጸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ትምህርት የሀገር መለወጫ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ባለፉት ሀምሳ አመታት ባለሀብቱንና የአከባቢው ህብረተሰብ በመተባበር የቆጠር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማሻሻል የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሚደነቁ ናቸው፡፡

በትምህርት ቤቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች፣ ቤተ-መጽሃፍት፣ ቤተ-ሙከራ፣ የመማሪያ ክፍሎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የተማሉ በመሆናቸው ከዞኑ አልፎ በክልል ደረጃ ሞዴል ሊሆን የሚያስችሉ ስራዎችን መሰራታቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በአግባቡ በአካባቢው ልማት በማሳተፍ ከፍተኛ የልማት ስራዎች ያለመንግስት እርዳታ ማከናወን እንደሚቻል በቆጠር ገድራ ትምህርት ቤት የተከናወኑ የልማት ስራዎች አይነተኛ ማሳያ መሆናቸውን አቶ ላጫ ጋሩማ ገልጸዋል፡፡

በዞኑ የትምህርት ጥራት ለማሻሻል በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው በተለይ ህጻናት በአፍ መፍቻ የጉራጊኛ ቋንቋ እንዲማሩ አበረታች ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የጉራጊኛ ቋንቋ የትምህርትና የስራ ቋንቋ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው በወረዳው የመንግስትና የህብረተሰቡ አቅም በማስተባበር በርካታ የልማት ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን የትምህርት ልማት ስራ ለማጠናከር ያለመንግስት ድጋፍ 42 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገንባት የትምህርት ቁሳቁስና መሰረተ ልማቶች በማሟላት ለትውድል በማስተላለፍ አርዓያነት ያላቸው ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች፣ የምህራን መኖሪያ ቤቶች ግንባታና ነባር የመማሪ ክፍሎች እድሳት በማጠናቀቅ ተመርቆ ለአገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡

የበዓሉ ተሳታፊ የድሞ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት የቆጠር ገድራ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለፉት ሀምሳ አመታት ሀገራቸውን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማገልገል ላይ የሚገኙ በርካታ ምሁራን ያፈራ የሀገር ባለውለታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ ትምህርት ቤቱ እውቀት ያላቸው በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎች እንዲያፈራ አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *