ፐብሊክ ሰርቫንቱ የአገልጋይነት ስነ ምግባር በመላበስ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት መስራትእንዳለበት የጉራጌ ዞን ፐብሉክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ።


ፐብሊክ ሰርቫንቱ የአገልጋይነት ስነ ምግባር በመላበስ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት መስራት
እንዳለበት የጉራጌ ዞን ፐብሉክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ።

መምሪያው በአገልጋይ መር ሚናና የሰራተኛው የስራ ቁርጠኝነት እና በመንግስት አገልግሎት ስነ ምግባርና እሴት ግንባታ ላይ ከሁሉም መምሪያዎች ለተወጣጡ ለሰው ሃብትና ለልማት እቅድ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ በስልጠናው ወቅት እንዳሉት የስልጠናው አላማ ሰልጣኞች ያገኙትን ስልጠና በቀጣይ በየመምሪያው ላሉ ባለሙያዎች በማሰልጠን ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው።

ሲቪል ሰርቫንቱ በስነ ምግባር በመታነጽ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ሰልጣኞችም ያገኙትን እወረቀት ተጠቅመው በተቋሞቻቸው ላሉ ባለሙያዎች ስልጠናው በተገቢው መስጠት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

በዞኑ በስነ ምግባር የታነጹ ፐብሊክ ሰርቫንት በማፍራት ህብረተሰቡን የሚፈልገው አገልግሎት እንዲያገኝና በልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መምሪያው ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

ለዚህም አመራሩና ፐብሊክ ሰርቫንቱ የአሰራር ስርአቶችን ተከትሎ ተግባራት እንዲፈጸሙ ለማድረግና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል መምሪያው በየጊዜው ስልጠና እየሰጠ መሆኑንም አመላክተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው የሚያነቃቃና ግንዛቤ እንዳገኙበት ገልጸዋል።

መምሪያው መሰል አይነት ስልጠናዎችን በየጊዜው ለፐብሊክ ሰርቫንቱ በመስጠት ያለባቸውን የክህሎትና የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እያደረገው ያለው ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ሰልጣኞችም ያገኙትን ስልጠና በተገቢው በመጠቀም በየሴክተር መስሪያ ቤት ላሉ ባለሙያዎች ስልጠናው እንደሚሰጡ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *