የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ተወላጅ አመራሮች ጋር በሁለቱም ዞኖች ሰላምና ልማት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በቡታጅራ ከተማ እያካሄዱ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ተወላጅ አመራሮች ጋር በሁለቱም ዞኖች ሰላምና ልማት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በቡታጅራ ከተማ እያካሄዱ ነው።

መድረኩ ፓርቲያችን መሪያችን ህዝባችን ደጀናችን በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር ውህደት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በመድረኩ ላይ እንዳሉት አመራሩ የተግባርና የአመለካከት አንድነት በመፍጠር የህብረተሰቡ ልማትና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል።

በአመለካከትና በተግባር የተግባባ አመራር ስልጣን በአግባቡ በመጠቀም ለህብረተሰብ ልማት ቀን ከሌሊት የሚተጋ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦች ልማት፣ ነጻነትና የእኩልነት ፍላጎት በዘላቂነት የተሟላበት፤ በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ህብረብሔራዊ አንድነትና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየሰራ ይገኛል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *