የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አበረታች መሆናቸውን የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ።


በጌታ ወረዳ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በመስክ ምልከታው ወቅት እንዳሉት በወረዳው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በግብርና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች ናቸው።

የአርሶ አደሩ ህይወት ለመቀየርና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ለማሳደግ በወረዳው በግብርና ዘርፍ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የአርሶ አደሩ ሀብት የሆነው መሬት ለመጠበቅ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በወረዳው በሌማት ትሩፋት አርሶአደሮችና የተደራጁ ወጣቶች ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች በማርባት የወተት ተጠቃሚነት ላይ፣ ዘመናዊና ባህላዊ የንብ ቀፎ በመጠቀም የማር ልማት ስራ፣ የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትና የሆነው እንሰት፣ እንዲሁም አርሶ አደሩ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት የሚለውን በተጨባጭ ያዩት ስራዎችን የበለጠ በማስፋት መስራት ይገባል ብለዋል።

አክለውም በወረዳው የትምህርት መሰረተ ልማት ለሟሟላት የመማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የመጸሀፍ አቅርቦት ጨምሮ በትምህርት ዘርፍ የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡን በማሳተፍ ቀበሌ ከቀበሌና ወረዳው ከአጎራባች ወረዳዎች ለማስተሳሰር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።

የቋንጤ ከተማ ለማሳደግ መሰረተ ልማት ለሟሟላት አመራሩና የመንግስት ሰራተኛው ደሞዛቸውን በመስጠትና ህብረተሰቡን በማቀናጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ውጤታማ ስራ ማየታቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አበረታች መሆኑን ገልጸው እነዚህን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በበኩላቸው በወረዳው በመንግስትና በህበረተሰብ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራቶችን ህብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

እንደ አቶ ክብሩ ፈቀደ ገለጻ የወረዳው ውስን በጀት በተገቢው በመጠቀም በከተማው የመንግስት ቢሮ ግንባታ፣ የዲችና የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ብሎም በገጠር ቀበሌያት በማህበረሰብ ተሳትፎ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን አድንቀው ይህም በወረዳው የህብረተሰቡ አቅም ሀብት አድርጎ በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ብለዋል።

በዚህም መንግስት ህብረተሰቡን ሀብት አድጎ በቅንጅት የተሰራው ስራ ወደ ሌሎችም አካባቢ አስፍቶ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲን በወረዳው ማህበረሰቡ፣ መንግስትና የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶችን በመተባበር በትምህርት መሰረተ ልማት፣ በመንገድ ልማት፣ በከተማ መሰረተ ልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን እየተሰሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል።

በወረዳው በትምህርት ዘርፍ የቡራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለት ብሎክ ግንባታ፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ስራዎችን፣ በግብርና ዘርፍ የጠረጴዛማ እርከን፣ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የችግኝ ጣቢያ፣ የበልግ ስራ የድንች ማሳ፣ የከተማው የፈርጅ ለውጥ ለማድረግ የወረዳው አመራር፣ ባለሙያዎችና ተወላጅ ባለሀብቶች በመቀናጀት የቋንጤ ከተማ የዲችና የጌጠኛ ንጣፍ ድንጋይ ብሎም የአስተዳደር ህንጻና የማዘጋጃ ቤት ግንባታ መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የወረዳው ህብረተሰብ ለልማት እያደረገ ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደረገ መጥቷል ያሉት አቶ በህሩ የመንግስት የውስጥ አቅም በተገቢው በመጠቀም ህብረተሰቡን በሁሉም ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመስክ ምልከታው የተገኙ ተሳታፊዎች እንዳሉት በወረዳው በግብርና፣ በትምህርት ዝርፎችና በመሰረተ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

የወረዳው መንግስትናህብረተሰቡ በመቀናጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስትን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *