አመራሩ እና አባሉ ህባችንን በማሳተፍና አቅም በማድረግ የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ለውጦች እየታዩ መሆኑን በመገምገም፤ ይበጥ እንዲጠናከር በቀሪ ወራት ርብርብ በሚፈልጉ የልማት፣የመልካም አስተዳደርና የጸጥታ ስራዎች ዙሪያ ከአመራሩ ጋር በመወያየት በሁሉም መስኮች ውጤታማነት ይበልጥ ይረጋገጥ ዘንድ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ፓርቲ ጽህፈት ቤቱ በዞኑ በግብርና፣ በማዓጤመ፣በተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍት ህትመት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በሰላምና ጸጥታ ስራዎች እንዲሁም የኑሮ ውድነት ለማቃለል በሚረዳ መልኩ በየመዋቅሩ የሰንበት ገበያዎችን በመፍጠር አምራቹና ሸማቹ ቀጥታ ለማገናኘት አመራራችን መላውን ህዝባችን በማሳተፍ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ገምግሞዓል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በመድረኩ እንዳሉት በዞኑ በበጀት አመቱ ከዋናው መሪ ዕቅድ ጎን ለጎን የአንደኛና በሁለተኛው ዙር የ100 ቀን ዕቅድ በማቀድ በተከናወኑ ተግባራት ላይ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

በዞኑ በግብርናው ዘርፍ በሁሉም አካባቢ ምንም ያልታረሰ መሬት እንዳይኖር ለማድረግ 5000ሄ/ር በአዲስ መልኩ ለማሳረስ እንደሚሰራ ያነሱት አቶ ክብሩ ለዚህም ውጤታማነት አመራሩ እና አባላችን መላውን አርሶአደር በማነቃነቅ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዞኑ የሚያመነጨውን ግብርን በተገቢው ለመሰብሰብ የገቢ ስርዓቱን በማዘመን እና በየደረጃው የሚታዩ ማነቆዎች በመፍታት እንዲሁም በዘርፉ ሚስተዋሉ ብልሹ አስተሳሰብና ተግባራት በማረም የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ውጤታማ ለማድረግ አባላችን አርዓያ በማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዞኑ በሁሉም አካባቢ የመቻቻል እና የአብሮነት እሴት በማሳደግና በየደረጃው ያሉ የጸጥታ ምክር ቤት ፎረም በማጠናከር ሰላም ለማረጋገጥ አመራሩ እና አባሉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታልም ብለዋል።

የወጣት ስራ ዕድል ፈጠራ ማነቆ በመፍታት የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እና በዘርፉ የሚስተዋለው ብድርን በወቅቱ ያለመመለስ ችግር ማረም እንደሚገባ ጠቁመው። በቀሪ ጊዜያትም ለተግባሩ ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከፓርቲ ስራዎች አንጻር አመራራችንና አባላችን የፓርቲው መመሪያና ዲሲፕሊን በመከተል፣ ፕሮግራሙ ወደ ውጤት በመቀየር፣ የህዝባችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥ፣ ብልጽግናን በተግባር እያሳየ ያለውን ህዝባችን ይበልጥ እንደአቅም ተጠቅመን ዞናችን በሁሉም ዘርፍ ሞዴል እንዲሆን መስራትና ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት የመፍጠሩ ስራ ይበልጥ ማጠናከር ይጠበቅብናል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በታክስ አሰባሰብ፣ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች የታቀዱ እቅዶችን ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅት ሊሰራ ይገባል።

በግብርናው ዘርፍ ያልታረሱ መሬቶችን ወደ እርሻ ማስገባት ላይ ሁሉም ተግባሩ በትኩረት መስራት እንዳለበት ጠቅሰው ከዚህም ባለፈ የሌማት ትሩፋት በገጠርና በከተማ አጠናክሮ ከበመስራት ባለፈ በትምህርት በጤናው በሌሎችም ዘርፎች ላይ አመራሩ በትኩረት በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት እንዳለበትም ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *