ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ምመሪያ አስታወቀ።

ህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃዎችን በማጥራት ዞኑ ኮፎርጂድ ዶክመንት ነጻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል።

መምሪያው ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤቶች አመራሮችና የማኔጅመንት አካላት ጋር በ2016 የግማሽ አመት ተግባር አፈጻጸም ላይ በወልቂጤ ከተማ መክሯል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ምመሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደተናገሩት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም በዞኑ በየመዋቅሩ በውስጥና በውጭ ተለይተው የታቀዱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ከዞን አስተዳደር ጋር በመሆን ግብረ ሀይል መዋቀሩ አስታውቀዋል።

ወ/ሮ ትብለጥ አክለውም በዞኑ ፎሮጂድ ዶክመንቶችን የማጥራት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ቀጣይ ከ14 ሺህ በላይ የትምህርት ማስረጃዎች ለማጥራት በትኩረት እየተሰራበት መሆኑ አመላክተዋል።

የቀበሌ ስራ አስከያጆች የአካባቢው ማህበረሰብ የሚፈልጋቸው አገልግሎቶች ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚገባቸው የተናገሩት ወ/ሮ ትብለጥ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እንዲደረግላቸው አስገንዝበዋል።

ፐብሊክ ሰርቫንቱ የሚጠይቃቸው በርካታ የጥቅማ ጥቅምና ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አዲስ ፖሊሲ እየተጠና ሲሆን ለችግሮቹም ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡ ከተቋሙ አጥጋቢ አገልግሎት እንዲያገኝ፣የ1ለ5ና የማኔጅመንት ውይይቶች፣የሪፎርም፣የኢንስፔክሽን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ተግባራቶች አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

እንደ ትብለጥ እስጢፋኖስ ገለጻ የሚደረጉ ምደባዎችን፣መዘናዎች፣ቅጥሮች፣ደረጃ የማሻሻልና ሌሎችም ተግባራቶች በተቀመጡ በመመረያዎች መሰረት ብቻ መሆን እንዳለባቸው መክረዋል።

የመምሪያው የሪፍርም፣ክትትልና ድጋፍ ዳይሮክተሬት የሆኑት በአቶ ተሰማ ተስፋዬ በ6 ወሩ ውስጥ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደገለጹት በዞኑ እየተስተዋለ ያለው የፎርጂድ ዶክመንት አሰራር ለማስወገድ ዶክመንቶችን የማጥራት፣ህገ ወጦችን እርምጃ እንዲወሰድባቸው እና ሌሎችም ሲያከናዉኑ እንደነበር አስታውቀዋል።

በቀጣይም ዞኑ ከፎርጂድ ዶክመንት ነጻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በኃላፊነት እንደሚሰሩ የተናገሩት ሀሳብ ሰጪዎቹ ለመንግስት ሰራተኛው የሚመጡ የትምህርት እድሎች፣ምደባዎች፣ቅጥሮች እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል።

የቀበሌ ስራ አስከያጆች ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጡ እንሰራለን ያሉ ሲሆን በተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *