በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መንግስት እንዲፈታላቸው የከተማው ነዋሪዎች ጠየቁ።

የከተማው ነዋሪዎች ሰላም እንዳይረጋገጥ ምክንያት የሆነውን የከተማው የወሰን አስተዳደር ጣልቃ ገብነት በአፋጣኝ እንዲወገድ በመድረኩ ተገለጸ።

በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው የህዝብ ውይይት ላይ የተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች እንደተናገሩት በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በሀገር ደረጃ በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።

በአዲስ አበባ የአድዋ ሙዚየም መገንባቱ አባቶቻችን የፈጸሙት የጀግንነት ተግባር ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ እና የሀገሪቱን አንድነት ለማጠናከር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ሰላም እንዳይረጋገጥ ምክንያት የሆነውን የወልቂጤ ከተማ የወሰን አስተዳደር ጣልቃ ገብነት እንዲወገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት እንዲቀረፍ፣ የመብራት መቆራረጥ ችግር የሆኑትን ያረጁ የእንጨት ፓል በኮንኩሪት ፓል እንዲቀየር፣ በከተማው የሚያቋርጠው አስፋልት መንገድ በማስፋት አከፋፋይ እንዲሆን ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ የተለያዩ ፋብሪካዎችና የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ ከዚህ ቀደም የተጠናው የዋቤ ወንዝ ገድቦ ለልማት እንዲውል የማድረግ ስራ እና የመብራት መቆራረጥ ችግር በቅርበት እንዲፈታ የመብራት ዲስትሪት በወልቂጤ ከተማ እንዲከፈት ጠይቋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም ማርሻሎና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ በውይይት መድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች በጋራ በሰጡት ምላሽ ህዝቡ ያነሳቸውን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው የሚገኘው የመንግሰት መዋቅር ደረጃ በደረጃ እንዲፈታ ታቅዶ ይሰራል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *