በማረቆና በመስቃን ህዝቦች በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን አካባቢ በተፈጠረ ያለመግባባት የእርቀ ሰላም ማፅናትን ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

በፕሮግራሙ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የክልሉ የህሄረሰብ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አበቶ አኒቶ፣ የክልሉ፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፤የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት የእርቅ ሰላም ስምምነት የማፅናት ፕሮግራም እየተከናወነ ይገኛል።

ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በባህላዊ የዳኝነት ስርዓት በተለያዩ ሁነቶች በማከናወን የእርቀ ሰላሙን ማፅናት ስራዎች ተሰርተዋል።

በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ፕርግራም እየተከናወነ ሲሆን በፕሮግራሙ አጠቃላይ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን ያከናወናቸውን ተግባራት ፣የሃገር ሽማግሌዎች የእርቀ ሰላሙ አጠቃላይ ሂደቱ ምን እነደነበር ያቀርባሉ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሰላምና የእርቀ ሰላሙን ሂደት አስመልክቶ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN
ቲዊተር https://twitter.com/home?utm_source=liteAPK&utm_medium=shortcut&first_run=false

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *