የተቀናጀ የበጋ የግብርና ልማት ስራዎች ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ በጉራጌ ዞን በጉንችሬ ከተማ ተካሄደ።

ጥር

በዞኑ ከ67 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተቀናጀ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሰራ እንደሚሸፈንም ተመላክቷል።

በጉንችሬ ከተማ በሀጅ አሊ ግጥም እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የሌማት ትሩፋት ተጎብኝተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የዘንድሮ አመት የተፈሰስና የበልግ ስራዎች ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተዉ እንዳሉት

በጉንችሬ ከተማ የጎበኙት የሌማት ቱሩፋት ስራዎች ሞዴልና በወተት በዶሮ እርባታና በሰጋ ፣በንብ እርባታ በከተሞች በደንብ ማስፋፋት እንደደሚቻል ያዩበት ጉብኝት እንደሆነም አመላክተዉ ከተሞችም በዚህም ልምድ ሊወስዱበት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ባለፉት አስር አመታት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሰራዎች በርካታ ለዉጦች የመጡ ሲሆን ይህንንም በዘንድሮ አመትም አጠናከሮ ለማስቀጠል በዞኑ አስፈላጊዉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የበልግ ስራዎች ዉጤታማ ለማድረግ በቂ ዉይይት ተደርጎ ያሉ መሬቶችን በተገቢዉ በማረስ የተሻለ ዉጤት በማምጣት ክልሉና ዞኑ የሚያስጠሩ ስራዎች መሰራት እንዳለበትም አደራ ሰጥተዋል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በንቅናቄ መድረኩ እንዳሉት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ፣ የበልግ ልማት ፣ የሌማት ቱሩፋት የፍራፍሬና የቡና ልመት ስራዎች በተቀናጀ መንገድ የአርሶአደሩ ህይወት በሚቀይር መልኩ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል።

በአምና ደረጃ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የእቅዱ መቶ ፐርሰንት ማሳካት መቻሉም አሰታዉሰዉ በዘንድሮ አመት 270 ንዑሰ ተፋሰሶች የተለዩና በዚህም 67 ሺህ 1 መቶ 25 ሄክታር በተለያዩ እስትራክቸሮች የሚለማ እንደሆነም አመላክተዋል።

በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ከምርት ዉጭ የነበሩ መሬቶች ወደ ምርት የመናስገባበት ሰይንሳዊ ዘዴ እንደሆነም አስረድተዉ የዞኑ የመሬት አቀማመጥና ስነ ምህዳር መነሻ ያደረገ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ዉጤታማ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል።

በዘንድሮ አመት በሁሉም ወረዳዎች 67 ሺህ 1 መቶ 25 ሄክታር መሬት የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሰራዎች ለማሳካት ግብ ተጥሎ በቅንጅት እንደሚሰራም አብራርተዋል።

በዚህም ከ3 መቶ 85 ሺህ በላይ አርሶአደሮች ፣ ወጣቶች ፣ሴቶች በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዉ ለ30 ቀን የሚሳተፉ እንደሆነም የተናገሩት አቶ አበራ ከምርት ዉጪ የነበሩ ማሰዎች ወደ ምርት በማስገባት የማሳ ሸፋን ማሰደግ እንደሚገባም አብራርተዋል።

የ2016/ 2017 የበልግ ልማት ስራ ከአምናዉ በተሻለ መልኩ ታቅዶ የሚሰራበት እንደሆነም አብራርተዉ በዘንድሮ አመት በአዘርትና በሆልቲካልቸር ስራዎች 67 ሺህ 2መቶ 87 ሄክታር ማሳ ለማልማት እቅድ መያዙም ተናግረዉ በዚህም ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት የሚጠበቅ መሆኑም አስታዉቀዋል።

በዞኑ በዋናነት የበቆሎና የድንች ምርቶች ትልቁ የማሳ ሽፋን የሚይዙ እንደሆነም ተናግረዉ የምርታማነት አቅማቸዋ በጣም ከፍተኛ የሆኑ ሰብሎችም እንደሆኑም አመላክተዋል።
የተቀናጀ የመሰኖ ልማት ሰራ

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ተጠቃሚነቱ በዘላቂነት ለማረጋገጥ በዘንድሮ አመት የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ሰራዎች በ2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በዘንድሮ አመት ከ7 መቶ 80 ሺህ በላይ የአቮካዶ ፣ የሙዝ፣ የአፕል ችግኞች በዘኑ አልሚ በሆኑ አርሶአደሮች ማሳ የሚተከል እንደሆነም አሰታዉቀዋል።

በጉንችሬ ከተማ ዛሬ የተጎበኘዉ የ30 40 30 የፍራፍሬ አካል የሆነዉ የሀጅ አሊ ግጥም የሌማት ቱሩፋት በከተሞችና ወረዳዎች ቢሰራ እንዴት ዉጤት ማምጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ሞዴል ሰራ እንደሆነም አመላክተዉ የህንንም ወደ ሌሎች ዌዳዎችና ከተሞች ማስፋት እንደሚገባም አብራርተዋል።

የወተት ሀብት ልማት ስራዎች በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እያደገ መምጣቱም አመላክተዉ የወተት አቅርቦቱ ማሳደግ እንደሚገባ ቷጉንችሬ ከተማ የሀጅ አሊ የወተት ምርታማነት ወደ ሌሎችም አርሶአደሮች ለሲፋ የሚገባዉ ተስፋ ሰጪ ስራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ስነ ምህዳሩን መሰረት ያደረገ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል በበኩላቸው የአርሶአደሩን ኑሮ ለማሻሻልና የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

እንፈልጋለን አቶ አለማየሁ ገለጻ በግልና በባለሀብቶች ሳይታረሱ ታጥረው የቆዩ ቦታዎች ለእርሻ አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ ይገባል።

የእኖር ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መብረቱ ተክሌ በኩላቸዉ ባለፉት አስር አመታት በወረዳዉ በተከናወኑ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሰራዎች በርከታ ለዉጦች በማምጣት የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል ተችሏል ብለዋል።

የተጎዱ መሬቶች አገግመዉ ዛሬ ላይ ምርት እየሰጡ እንደሆነም አመላክተዉ በዘንድሮ አመት በወረዳዉ በዘንድሮ አመት 10 ሺ በላይ ሄክታር መሬት በተፋሰስ ልማት ለማልማት ግብ ይዘዉ እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የከተማ ግብርና ሀላፊ አቶ መሀመድ ተማም እንዳሉት በከተማዉ በርካታ በግልና በማህበር ተደራጅተዉ በወተት ምርት ፣በአንድ ቀን ጫጩት ምርት ፣በዶሮና በሌሎችም ሰራዎች ተሰማርተዉ ያሉባቸዉን ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸዉ እየቀረፉ አንደሆነም አስረድተዋል።

በጉንችሬ ከተማ በከተማ ግብርና ሰራ የተሰመሩ ሀጅ አሊ ግጥም እንዳሉት ከአንድ ከብት ጀምረዉ ዛሬ ወደ 45 ከብቶች በማሳደግና ለአካባቢዉ ማህበረሰብ በቀን ከ 160 ሊትር በላይ የወተት ምርት ለከተማዉ ማህበረሰብ እያቀረቡ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከዚህም ጎን ለጎን የቡና ፣የሙዝ ፣ የአቮካዶና ሌሎችም የፍራፍሬ ዉጤቶች እያለሙ እንደሆነም አስረድተዋል ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *