ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2015 የመስቀል በዓል አደረሳችሁ አያለ በዓሉ የሠላም፣የፍቅርና የደሰታ እንዲሆን የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ መልካም ምኞቱን ይገጻለል።

መስከረም 12 /2015 ዓ/ም

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2015 የመስቀል በዓል አደረሳችሁ አያለ በዓሉ የሠላም፣የፍቅርና የደሰታ እንዲሆን የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ መልካም ምኞቱን ይገጻለል።

ወኼም ቦኼ የጉራጌ ወኸመያ አሠናናሁም
ወኼ ሙራ የህር !!!

መምሪያው የመስቀል በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ዞኑ የሚመጡ የእምነቱ ተከታዮች ለአላስፈላጊ የዋጋ ጭምሪ እንዳይደረግ ለመከላከል ከተያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሠሩ መሆኑን ገልጿል።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ በሀገራችን ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱና ዋነኛ የመስቀል በዓል ሲሆን በተለይም በጉራጌ ዞን በአሉ በልዩ ድምቀት የሚከበር በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የዞኑ ተወላጅ የእምነቱ ተከታዮችና ሌሎችም እንግዶች በዓሉን ለማክበር ወደ ዞኑ በብዛት ይመጣሉ ብለዋል።

ለበአሉ ሲመጡም ሆነ ከበዓል በኋላ ሲመለሱ ህብረተሠቡ ለአላስፈላጊ የትራንስፖርት ወጪ
እንዳይዳረግ ከተለያዩ ከአጎራባች ዞኖችና ከፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ጋር በመተባበር ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሠራቱን አብራርተዋል ።

ይህም ከዚህ በፊት እንደተለመደው ሳይሆን በአስፓልትና በጠጠር መንገድ በኬሎሜትር የወቅቱ የነዳጅ ገበያ ዋጋን ያገናዘበ የበዓል ልዮ ታሪፍ ከዚህ በታች በተለጠፈዉ መሠረት መሆኑን ለሚመለከተው ሁሉ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።

የተጋነነ ክፍያን ችግር ለመቆጣጠርና የትራፊክ ፍሰቱ ጤናማ እንዲሆን ከኦሮሚያ ክልል ከደቡብ ምዕራብ ዞን፣ ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር ፣ከአዲስ አበባ፣ከፌደራል መንገድ ትራንስፖርትና ከሌሎች ከአጎራባች ዞኖች ጋር በመተባበር ሰፊ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል ።

ህብረተሠቡም ከመነሻ አሰከ መድረሻው ያለውን ርቀት በኪሎሜትር በወጣው ታሪፍ መሠረተ የደርሶ መልስ በመክፈል እራሱን ከአላስፈላጊ ወጪ መከላከል ይገባል ብለዎል።

ከዚህ በተለየ መልኩ በተጓዦች የተጋነነ የታሪፍ ጭማሪ የሚያስከፍሉ ፣ከተፈቀደላቸው ወጪ ትርፍ የሚጭኑና ሌሎች ችግሮች ሲገጥሙት በየመስመሩ ለተሠየሙ የመንገድ ትራፊክ ፖለስና ለመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ባለሞያዎች ጥቆማ በመስጠት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የመንገዶች መቦርቦ ብልሽት ለትራፊ አደጋ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ ስላለው በዋና ዋና መንገዶች ከሚያቋርጧቸው ወረዳዎች ጋር በመናገር ጊዜያዊ ጥገና መሠራቱን ገልፀዋል።

የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው በወልቂጤና ሌሎች ከተሞች አማራጭ ተለዋጭ መንገድ የማመቻቸት ፣ባጃጆች ከዋናው መንገድ እንዲወጡ ለማድረግ ግንዛቤ የመፍጠርና ስራ መሠራቱና ለተፈፃሚነቱ ከትራፊክ ፓሊስ በተጨማሪ የተማሪ ትራፊ ክበብ አባላትና በጎፈቃደኛ ወጣቶች በማሳተፍ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በበዓሉ ምክንያት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና መጨናቅ በሚኖርባቸው በወልቂጤ፣በቡታጀራ ፣በቡኢና በሌሎች መስመሮች የተጠናከረ ቁጥጥር ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በድጋሜ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሠላም፣የፍቅርና የደሰታ እንዲሆንላቸውን ተመኝተዋል።
መግለጫውን ተከታትሎ ያደረሳችሁ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *