አቅም የሌላቸው ተማሪዎችንና የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ ።

መስከረም 9/2015

አቅም የሌላቸው ተማሪዎችንና የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ ።

በዛሬዉ እለት በወረዳና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ለመማር አቅም ለሌላቸው ለ 32 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አመተረኡፍ ሁሴን እንደገለጹት ድጋፉ የተደረገላቸው ወላጅ የሌላቸው፣በችግር ውስጥ የሚገኙና ቤተሰቦቻቸው ማስተማር የማይችሉ ተማሪዎች መሆኑን አብራርተዋል ።

በክርምት ወቅት ጀምሮ እስካሁን 16 ሺህ 8 መቶ 79 ለመማር አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች በማህበረሰቡና የተለያዩ ድርጅቶች በማስተባበር የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል ።

ኃላፊዋ አክለውም ድጋፍ ከተደረጉት መካከል 1 ሺህ 1መቶ 12 የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ 2 ሺህ 1 መቶ 58 ፓኬት እስክርቢቶ ፣16 ሺህ 1መቶ 99 ደርዘን ደብተር ፣ 2 መቶ 35 ቦርሳ ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናትና ወጣት ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉን ተናግርዋል ።

እንዲሁም በክረምት በጎ ፍቃድ ጋር በማስተሳሰር 6 መቶ 89 ቤቶች እድሳትና አፍርሶ ግንባታ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያንና ለሌሎች አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መሰራቱን ው/ሮ አመተሩፍ አመላክተዋል ።

መምሪያው ቀደም ባሉት ጊዜያት ጀምሮ ለመማር አቅም የሌላቸው ተማሪዎችን አስተምሮ ወደ ስራ አለም የገቡ እንዳሉ ገልጸው አሁንም በቋሚነት 5 ተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁስ፣የአልባሳት፣ የደንብልብስና ለምግብነት የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

በዛሬዉ እለትም በቀቤና ወረዳ፣ በወልቂጤ ከተማና በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለሚገኙ ለመማር አቅም ሌላቸው ለ ሰላሳ ሁለት ተማሪዎች በላይ ለእያንዳንዳቸው 6 ደብተርና እስክርቢቶ በዛሬው እለት ድጋፍ ተደርጓል።
የዞናችን ማህበረሰብና ረጂ ድርጅቶች በየአካባቢው ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች መርዳት እንዳለባቸው ወይዘሮ አመተረኡፍ ሁሴን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በበኩላቸው እንዳሉት መምሪያው ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያስፈልጋቸው አመላክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *