የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማሻሻል የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝ በወልቂጤ ከተማ የእድገት በር ጤና ጣቢያ አስታወቀ።

መስከረም 9/2015

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማሻሻል የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝ በወልቂጤ ከተማ የእድገት በር ጤና ጣቢያ አስታወቀ።

የጤና ጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይብጌታ እንደገለጹት ጤና ጣቢያው ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት እየሰራ ይገኛል ።

ጤና ጣቢያው ከከተማው ባሻገር ከአጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚሚመጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል ።

ጤና ጣቢያው የወሊድ፣ የተመላላሽ፣ የድንገተኛ ህክምናና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን በህክምና መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ከበደ ገልጸዋል።

የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤናቸውን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ከበደ እናቶች የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድና የድህረ ወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።

በ2014 ዓ.ም በከተማውና አጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ ነፍሰጡር እናቶች ከመለየት ባሻገር በሰለጠነ ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ ግንዛቤ ይፈጠርላቸዋል።

አንዲት ነፍሰጡር እናት እስክትወልድ ጤና ጣቢያው ከአንድ ሺህ ብር በላይ ወጪ የሚያወጣ በመሆኑም ጤና ጣቢያው የሚሰጠው አገልግሎት ጥራትና ተደራሽበት ለማሳደግ መንግስት ድጋፍ ማድረግ አለበት ብለዋል።

በጤና ጣቢያው ቅድመ ወሊድና የወሊድ አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች ቁጥር እየተሻሻለ ሲሆን በ2014 ዓም የመጀመሪያ የቅድመ ወሊድ ክትትል ካደረጉ እናቶች ከ550 በላይ የሚሆኑ እናቶች የቅድመ ወሊድ እና የወሊድ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል። አፈጻጸሙ ከ70 በመቶ በላይ መሆኑን በመግለፅ ።

በጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚሰጥባቸው ክፍሎች መጥበብና የእናቶች ማረፊያ ክፍሎች አለመኖራቸው በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ለማስፋፊያ ግንባታው ስራ ባለሀብቶች፣ የአካባቢው ማህበረሰብና መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል አቶ ከበደ።

በተቋሙ ውስጥ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ብቁ፣ ሩህሩህና ተገልጋይ አክባሪ ባለሙያዎች የሚገኙ ቢሆንም ያላቸው እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች መሟላት እንዳለባቸው አክለው ገልጸዋል ኃላፊው።

በጤና ጣቢያው ጠቅላላ ሀኪም ዶክተር ቤተልሔም ሽታ በበኩላቸው ጤና ጣቢያው ያለውን የሰው ሀይል እና ቁሳቁስ በመጠቀም ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችል እየተሰራ ሲሆን አገልግሎት ይበልጥ እንዲጠናከር የህክምና መሳሪያዎች እብዲሟሉ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

መቅደስ ተመስገን የእናቶችና ህጻናት ኬዝ ቲም አስተባባሪ ሲሆኑ የእናቶች ሞት ለመቀነስና የህጻናት ጤና ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ወይዘሮ አለምነሽ ግዛው በወልቂጤ ከተማ የእድገት በር ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ወይዘሮ አምሪያ አጫሉ ደግሞ በቀቤና ወረዳ የርሙጋ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ለህሙማን የሚሰጡት ክብርና የሚያደርጉት እንክብካቤ ከፍተኛ በመሆኑ ተቋሙ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ከባለሙያዎች ስነምግባር በተጨማሪ ተገልጋዮች ሳይጉላሉ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በተቋሙ የመድኃኒት እጥረት እንዳይከሰት እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *