የጉራጌ ዞን የትምህርት መክፈቻ ፕሮግራም በቸሀ ወረዳ አዘርና ሲሰ በሳህለማሪያም ንጋቱ መታሰቢያ ትምህርት ቤት እየተካሄደ ነው።

መስከረም 03/2015

የጉራጌ ዞን የትምህርት መክፈቻ ፕሮግራም በቸሀ ወረዳ አዘርና ሲሰ በሳህለማሪያም ንጋቱ መታሰቢያ ትምህርት ቤት እየተካሄደ ነው።

አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ብቁ ስራፈጣሪና በስነምግባር የታነፀ የሰው ሀይል ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን የሚገኙ ከ6መቶ በላይ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2015 እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት እና መደበኛ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ መስራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ።

ትምህርት በወቅቱ መጀመር ተማሪዎች በደረጃቸው ማግኘት የሚገባቸው እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በትምህርት ሳምንቱ “ሁሉም ለትምህርት፣ ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪቃል አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማልና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ፣ የቸሀ ወረዳ እና የእምድብር ከተማ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ዝርዝር መረጃው አጠናቅረን እናቀርባለን !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *