የእንቁጣጣሽ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዞኑ ለሚገኙ ለዘማች ቤተሰብና አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የበግና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

መስከረም 1/2015 ዓ.ም

የእንቁጣጣሽ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዞኑ ለሚገኙ ለዘማች ቤተሰብና አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የበግና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ማህበረሰቡ የመረዳዳት ባህሉን በማጎልበት የተጀመሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ፣ የወጣት አደረጃጀትና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በጋራ በመሆን ነው ደጋፍ የተደረገው።

የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አመተእሩፍ ሁሴን የተቸገሩ ወገኖችና የዘማች ቤተሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ተቸግረው እንዳያሳልፉ በማሰብ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

በዞኑ በክረምት ወራት ከ8ሺህ በላይ አረጋዊያን ፣7መቶ አካል ጉዳተኞች ፣ ከ10 ሺ በላይ ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናት ድጋፍ መደረጉ አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን በይበልጥ በማጠናከር የተቸገሩ አረጋውያንና አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በማሰብ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት ኃላፊዋ ቀጣይም የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍ እንክብካቤ ጥምረቶች እሰከ ቀበሌ ድረሰ ስላሉ ድጋፉ መጠናከር አለበት ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የወጣትች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ ለዘማች ቤተሰብና አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በግ፣ዘይት፣ ዶሮ ፣ ዱቄት ደጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን እስከ 80 ሺህ ብር እንደሆነ ገልጸዋል።

ከቤተሰቤ ሀገሬ ይበልጣል ብለው የሀገር ጉዳይ አሳስቦዋቸው መከላከያ የተቀላቀሉ አካላት ቤተሰቦች እንደማንኛውም ሰው ተደስተው እንዲያሳልፉ ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዘንድሮ በበጋና በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በተለይ በባዓላት ወቅት የኑሮ ውድነቱን በማሰብ 3መቶ 39 ሰንጋዎች ለተቸገሩትና ለዘማች ቤተሰብ መከፋፈሉ አስገንዘበዋል።

እንደ አብዶ ገለጻ ይህን ተግባር መስቀልን ጨምሮ በሌሎች ጊዜያትም ቀጣይነት እንደሚኖረው አስታውቀዋል።

ማህበረሰቡ የመረዳዳት ባህሉን በማጎልበት የተጀመሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ አብዶ ገልጸዋል።

ወይዘሮ ጌቱ ዳሬዶ ፣ወይዘሮ ዘይነባ አህመድና ወይዘሮ እቴነሽ ኤርመንጎ ድጋፍ የተደረገላቸው እናቶች ሲሆኑ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸው ተናግረዋል።

ቤታችን ውስጥ ምንም ባለመነኖሩና የኢኮኖሚ ችግር ስላለብን ለበዓሉ የሰው እጅ እየጠበቅን ነበር ያሉት ተረጂዎቹ አሁን ግን ባገኘነው ድጋፍ በአሉ በደስታ እንድናሳልፍ አድርጎናል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *