የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ተወካይና የዞኑ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ለጸጥታ አካላት ለ2015 ዓ. ም ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳቹሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጳጉሜ 4/2014 ዓ .ም

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ተወካይና የዞኑ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ለጸጥታ አካላት ለ2015 ዓ. ም ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳቹሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በየአካባቢዉ ህብረተሰቡ ሰላምና ጸጥታዉን እየጠበቀና በተጨማሪም የእሳት አደጋ ችግር እንዳይፈጠር ከመቼም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ እንዳይለየዉ።

በአሉ የሰላም ፣ የመተሳሰብ ፣የአብሮነት እንዲሁም ከተቸገሩ ወገኖችና ከዘማች ቤተሰብ ጋር በመሆን ልናከበረዉ ይገባል።

ባሳለፍነዉ አመት የ2014 ዓ.ም የዞናችን የጸጥታ መዋቅሩ ህዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በርካታ የጸጥታ ስራዎች ሲያከናዉን መቆየቱ ይታወቃል።

ባሳለፍነዉ አመት በዞናችን የጸጥታ ችግር የነበረባቸዉ አካባቢዎች ከህዝቡ ጋር በሰራናቸዉ ስራዎች አንጻራዊ ሰላም ማምጣት ተችሏል።

መጪዉ አዲስ አመት ብሩህ ተስፋ የምናይበት የተሻለና አንጸባራቂ ዉጤቶችን የምናስመዘግብበት የሀገራችን ብሎም የዞናችን ከፍታ የምናረጋግጥበት እንደሚሆን ታላቅ እምነት አለኝ።

የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር እየተዋደቀ ላለዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ ለሚሊሻ ሰራዊትና ለፖሊስ አባላቶች የክልሉ ልዩ ሃይል በድጋሚ እንኳን ለ2015 ዓ .ም ዘመን መለወጫ በአል በሰላም አደረሳቹሁ በማለት ምኞታቸዉን ገልጸዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የጸጥታ ሀይሎች ዝግጁ መሆናቸዉም ተናግረዋል።

    የጥቆማ ስልኮች 

0113300323: 0113300288
0113300258 : 0113658137

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *