በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 93 ቤቶች ለአቅመ ደካማና የአረጋውያን ወገኖች በአዲስ መገንባቱና ጥገና መደረጉ በጉራጌ ዞን የቸሀ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 93 ቤቶች ለአቅመ ደካማና የአረጋውያን ወገኖች በአዲስ መገንባቱና ጥገና መደረጉ በጉራጌ ዞን የቸሀ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአዲስ ግንባታና ጥገና የተደረገላቸው ቤቶች በወረዳዉ አመራሮች ተጎብኝቷል።

የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር ወጣቶችና ባለሀብቶችን በማስተባበርና የመንግስትን ጥቂት ድጋፍ በማከል 54 ቤቶችን አዲስ በመገንባትና 39 ቤቶችን ደግሞ እድሳት መደረጉን አብራርተዋል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 7 ሺህ 275 የሚሆኑ የወረዳዉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማስጠቀም መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም 16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ማዳን መቻሉንም አስረድተዋል።

የቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈታ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ14 ሺህ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል፣ 22 ዩኒት ደም የመለገስ፣ አልባሳት የማሰባሰብና ማዕድ የማጋራት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪ በወጣቶች በጎ ፈቃድ 39 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን አብራርተዋል።

በወረዳው የሚገኙ የ103 የዘማች ቤተሰብ ማሳን መንከባከብ ጨምሮ በህልውናው ዘመቻ ለተሰው ቤተሰቦች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ደሳለኝ ፈታ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *