በጉራጌ ዞን ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረጉት ያለዉን ድጋፍ አጠናክረዉ መቀጠላቸዉም ተገለጸ።

ጳጉሜ 3/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረጉት ያለዉን ድጋፍ አጠናክረዉ መቀጠላቸዉም ተገለጸ።

በዞኑ የሴቶች አደረጃጀት ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ደረቅ ምግብ፣ ሰንጋዎች፣ የፍየልና የበግ ሙክቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንደገለጹት ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም የበኩላቸዉን እየተወጡ ነው።

120 ኩንታል በሶ ፣ 48 የፍየልና የበግ ሙክቶች፣ 68 ሰንጋዎች በሴቶች አደረጃጀት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል።

በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ሴቶች በቡድንና በግል በመሆን በሀገር ጉዳይ እየተዋደቁ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት የሚያደርጉትም ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚያስቀጥሉም አስታዉቀዋል።

ሴቶች በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸዉን እየተወጡ ሲሆን ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የበሶ፣ የሰንጋ ፣ የፍየልና የበግ ሙክቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *