የጉራጌ ዞን ህብረተሰብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ከ30 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ሰንጋዎች፣ የበግና የፍየል ሙክቶችና ደረቅ ምግብ ለኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ለማስረከብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ህብረተሰብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ከ30 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ሰንጋዎች፣ የበግና የፍየል ሙክቶችና ደረቅ ምግብ ለኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ለማስረከብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በሀገር ሉአላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የዞኑ ህዝብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተገለጸ።

የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ የዞኑ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊት ያደረገውን ድጋፍ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ህውኋት ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት የዞኑ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ምግብ በማቅረብ፣ ወጣቶች በማሰለፍ፣ የዘማች ቤተሰብ መንከባከብ ፣ የአከባቢውን ሰላም መጠበቅ ሀገራዊ ግዴታውን ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል።

መንግስት የሰላም አማራጭ ቅዲሚያ በመስጠት ድርድር ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም አሸባሪው የህውኋት ቡድን ይህንን የሰላም ጥሪ እንደ ሽንፈት በመቁጠር ለ3ኛ ጊዜ ሀገሪቷ የወረረውን አሸባሪ እስኪደመሰስ ከመከላከያ ጎን በመቆም ህብረተሰቡ ደጀንነቱን እያሳየ ይገኛል።

ይህንን መነሻ በማድረግ የሽብር ቡድኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በቀረበው ጥሪ መሰረት

3 መቶ 73 ሰንጋዎች 1 መቶ 59 የበግና የፍየል ሙክቶች፣ 96 ኩንታል ስኳር፣ 1መቶ 20 ኩንታል በሶ ማሰባሰብ መቻሉን የገለጹት አቶ ክፍሌ ይህም በገንዘብ ሲተመን 30ሚሊዮን 624 ሺህ 675 ብር መሆኑን ተናግረዋል።

የአከባቢውን ሰላም በመጠበቅ፣ ሰርጎ ገቦች በመለየት በየትኛውም አከባቢ ለሰላም መደፍረስ ችግር የሚሆኑ አካላትን በአከባቢው ባህል፣ ወግና ልማድ መሰረት በመቅረፍ ለግንባር አጋዥ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር ህብረተሰቡ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አብድረዛቅ ወለላ በበኩላቸው በዞኑ አብይ ኮሚቴና ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማዋቀር በአጭር ቀናት የሰንጋ፣ የበግና የፍየል ሙክቶች፣ የበሶና የስኳር ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል።

የዞኑ ህዝብ በሀገር ሉአላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመከላከል በሚደረገው ስራ ላይ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም የሀገሪቷ ሰላም እስኪረጋገጥ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ሀገሪቷ የተጋረጠባትን የህልውና ጦርነት ለመቀልበስ በግንባር እየተፋለመ ያለው የዘማች ቤተሰብ የመደገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በተለይም በገጠር የማሳ እንክብካቤና በከተማ የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸውን ቤተሰብ በክረምንት የበጎ ፈቃድ ስራ በማስተሳሰር የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *