በቡታጅራ ማእከል ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሰንጋና በሶ መሰብሰቡ ተገለጸ::

ጳጉሜ 3/2014
በቡታጅራ ማእከል ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሰንጋና በሶ መሰብሰቡ ተገለጸ::

በማእከሉ 148 ሰንጋዎች ለመከላከያ ሰራዊት መሰብሰቡ ታውቋል።

በማእከሉ ሰንጋዎችን ያስረከቡት ፣የሶዶ፣የደቡብ ሶዶ፣የመስቃን፣የምስራቅ መስቃን፣የማረቆ፣የእንሴኖ፣፣የቡኢና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች ናቸው።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ የሀብት አሰባሰቡን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት የዞኑ ህዝብና መንግስት ሀገራችን ከገጠማት የውጭና የውስጥ ፈተና በድል ለመሻገር የበኩሉን እየተወጣ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከነዚህም 148 ሰንጋ፣62 ኩንታል በሶ፣17 ሙክት በግና ፍየል መረከባቸው አቶ አበራ ወንድሙ ተናግረዋል።

ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሰንጋና በሶ መሰብሰቡ አስገንዝበዋል።ከዚህ በፊት ለዚህ ተግባር ወጣቶች፣ሴቶች የግልና የመንግስተ ተቋማት ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።

አቶ አበራ አክለውም ማህበረሰቡ የህዋሀት ቡድን ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን እየሰጠ ሲሆን ይህ ደግሞ የጉራጌ ማህበረሰብ ለሀገር ከፍተኛ ፍቅር ያለውና በሀገር ጉዳይ የማይደራደር መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ቡታጅራ 43፣ ሶዶ 20፣ደቡብ ሶዶ14 ፣ምስራቅ መስቃን 15 ፣ቡኢ 9 ፣እንሴኖ 5፣ መስቃን 25 ፣ማረቆ 17 ሰንጋዎችን ማበርከታቸው አቶ አበራ አስታውቀዋል።

ሰራዊቱን በሞራልና በስንቅ ማገዝ እንደሚያስፈልግ ታሳቢ በማድረግ ይህ ተግባር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ ያደረጉ አመራሮችን ህብረተቡን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህን አሸባሪው የህዋሀት ቡድን ከሀገር እስኪጠፋ ድረስ ህብረተሰቡን የጀመረው ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸውን አስተላልፏልሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *