ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም

ያዶት የምግብ ኮምፕሌክስ የዱቄት ፋብሪካ በቀን 4 መቶ 20 ኩንታል ዱቄት ማምረት የሚያስችለውን አቅም ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።

በእምድብር ከተማ የተገነባው ያዶት የዱቄት ፋብሪካ በአሁኑ ሰዓት በአንድ ቀን 4 መቶ 20 ኩንታል ዱቄት ማምረት የሚያስችለውን አቅም ላይ እንደሚገኝ የፋብሪካው ባለቤት የሆኑት ወጣት አበጀ ሳህሌ ገልፀዋል።

የፈብሪካው ዓመታዊ የሰራተኞች በዓል በተግባር አፈፃፀም የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ሰራተኞች እና የፋብሪካው ዱቄት በብዛት ተጠቃሚ የሆነ ግለሰብ፣ ተረፈ ምርት ፉርሽካ በብዛት ገዢ እና የስንዴ ምርት አቅራቢዎችን የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ።

ያዶት የምግብ ኮምፕሌክስ የዱቄት ፋብሪካ ባለቤት የሆኑት ወጣት አበጀ ሳህሌ እንዳሉት የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተቀርፆ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ በመግለፅ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ መኮሮኒ፣ ፓስታና ብስኩት ማምረት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል።

በዚህ ጊዜ ፈብሪካው ከ1ሺ በላይ ሰራተኞችን መቅጠር እንደሚችል ወጣት አበጀ ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ ፋብሪካው ዱቄት ከማምረት ጎን ለጎን ከብት የማድለብ፣ ንብ የማነብ፣ የጓሮ አተክልት ማምረትና ለምግብነት የሚሆኑ ችግኞችን የመትከል ተግባርም ላይ እንደተሰማራ የፋብሪካው ባለቤት ገልጸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የእንድብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግንባሩ በርጋ እንዳሉት እንዲህ አይነት ትጉና ታታሪ ወጣት ባለሃብት ለሌሎችም ወጣቶች አርዓያ እንዲሆን በተቻለ ሁሉ ማበረታታት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ወጣት አበጀ ይህንን ፋብሪካ ሳቋቁም ላበረታቱኝ ለእምድብር ከተማ አስተዳደር አመራርና ማዘጋጃ ቤት ምስጋናቸውን በማቅረብ በሩንጨ፣በቃያና በፈረዝየ ቀበሌ ለሚገኙ ለ15 የድሃ ድሃ ቤተሰብ ተማሪዎች የደብተርና የእስክሪፕቶ ስጦታ አበርክተው የአካባቢው አርሷደር ከእንሰትና ከጫት ምርት በተጨማሪም ለፋብሪካው ግብዓት የሚሆን ስንዴ ማምረት እንዳለበት ጠይቀዋል።

መረጃው የእ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *