የበጎነት ባህላችን በማጎልበት የተቸገሩ ዜጎች ምቹና አስደሳች ህይወት እንዲኖሩ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።

ነሀሴ 28/2014 ዓ.ም
===============
የበጎነት ባህላችን በማጎልበት የተቸገሩ ዜጎች ምቹና አስደሳች ህይወት እንዲኖሩ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።

በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ በዋጮና በገነተ ማርያም ቀበሌዎች በወጣቶችና ስፖርት እና በሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤቶች ለሁለት አቅመ ደካማ አረጋዊያን አዲስ ቤት ገንብተው ማስረከባቸውን ገለጹ።

የሶዶ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ እንደተናገሩት በዋጮ ቀበሌ የአንዲት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ አቅመ ደካማ እናት አዲስ ቤት የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና የሴት አደረጃጀት ጋር በመተባበር ገንብተው ማስረከባቸውን ተናግረዋል።

ለዚህ ቤት ግንባታ የሶዶ ወረዳ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ፣ አቢሲኒያ፣ ኦሮሚያና ንብ ባንኮች ለቤቱ ግንባታ የሚውል ቁሳቁስ ማበርከታቸው ጠቁሟል።

በእለቱ የተከናወኑ ተግባራት በገንዘብ ሲተመን ከ30ሺህ በላይ እንሚገመት የተገለጸ ሲሆን ብለው በጎነት ከተረፈን ብቻ ሳይሆን ካለን ላይ ማካፈል በመሆኑ ሁላችንም ከተጋገዝን አቅመ ደካማ ዜጎች ምቹና ደስተኛ ህይወት እንዲኖሩ እንደሚያስችላቸው ኃላፊዋ ተናግረዋል።

የሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው ስዩም በገነተ ማሪያም ቀበሌ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወይዘሮ ለጋነሽ የቆርቆሮ ቤት ሰርተው ማስረከባቸውን ገለጹ።

በሶዶ ወረዳ ዋጮ ቀበሌ አዲስ ቤት የተገነባላቸው ወይዘሮ አዳነች ገብረ ወልድ የሰው መኖሪያ መሆን በማይችል ቤት ውስጥ ዝናብና ውርጩ እየተፈራረቀባቸው በስቃይ ይኖሩ ነበር ገልጸው በበጎ ፈቃድ አገልጎሎት አዲስ ቤት ተሰርቶላቸው ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስታቸውን ገልጸዋል ሲል የዘገበው የሶዶ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *