የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔ አስተላለፈ።

ነሐሴ 27/2014

የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔ አስተላለፈ።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ አፅንዖት ሰጥቶ መክሯል።

የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው 247ኛ መደበኛ ስብሰባው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል።

መንግስት ለሰላም ያለውን ፅኑ አቋም በተኩስ አቁም ያሳየ ሲሆን አርሶ አደሩ ከነበረበት የጦርነት ስጋት ወጥቶ ወደ ግብርና ስራው እንዲያተኩር ለማድረግ እና በሁሉም መስክ የሚከናወኑ ስራዎች እንዲቀጥሉ ለማድረግ መንግስት ሰላምን ማስቀደሙን መስተዳድር ምክርቤቱ በስፋት መክሮበታል።

ሆኖም ግን አሸባሪው ህወሀት መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት ወደ ጎን በመተው ለሶስተኛ ጊዜ በህዝብ ላይ ግልጽ ወረራ ፈፅሟል።

መንግስት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ብሎም በሀገሪቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ተገዶ የገባበትን ጦርነት መስተዳድር ምክር ቤቱ የሚደግፍ ሲሆን ሂደቱንም በቅርበት እንደሚከታተል አጽንኦት ሰጥቷል።

አሸባሪው ቡድን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እንዲሁም ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በማበር ሀገር ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ወረራ መስተዳድር ምክር ቤቱ አውግዟል።መንግስት አሁንም ቢሆን የሰላም አማራጮችን እያስቀደመ መሆኑን መስተዳድር ምክር ቤቱ በአድናቆት ተመልክቶታል።

የክልሉ ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ሀገርን ከጥቃት ለመከላከል የማይተካ ህይወታቸውን እየሰጡ ላሉት ጀግኖች ስንቅ በማዘጋጀት፣በግንባር በመዝመት፣፣የዘማች ቤተሰብን በመንከባከብ ፣የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ እንዲሁም በልማት ስራ ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ መስተዳድር ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

አሸባሪው ህወሀት እና አንዳንድ አፍራሽ መገናኛ ብዙሀን የሚያሰራጩትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ህብረተሰቡ ወደ ጎን በመተው መንግስት የሚያስተላልፋቸውን መልዕክቶች እንዲከታተል መስተዳድር ምክር ቤቱ አጽንኦት ሰጥቷል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምሥረታ እና ነባሩን ክልል በአዲስ ክልል የማደራጀት ተግባር ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማቋቋሚያና የአሰራር ሥርዓት መወሰኛ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል:: መረጃው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *