ለሰላም የተዘረጉ እጆችን ረግጦ በሀገራችን ላይ ወረራ በፈፀመዉ አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን የህልውና ዘመቻ እንደሚደግፉ አንዳንድ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ ።

ነሐሴ27/2014 ዓ.ም

ለሰላም የተዘረጉ እጆችን ረግጦ በሀገራችን ላይ ወረራ በፈፀመዉ አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን የህልውና ዘመቻ እንደሚደግፉ አንዳንድ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ ።

አስተያየት ከሰጡ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ንጉሱ ገቢና አቶ ጌትነት አበባው ለሰላም የተዘረጉ እጆችን ረግጦ ኢትዮጵያን ለመበታተን ወረራ የፈፀመው አሸባሪው የህወኋት ቡድን ላይ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት አየወሰደ ያለው አርምጃ ተገቢነት ያለው ነው ብለዋል።

በሀገር ላይ የሚመጣ ጠላት በጋራ የመደምሰስ ከአባቶቻችን የወረሰነው ታሪክ ስላለ በሚችሉት ሁሉ መስዋዕትነ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።

ይህ አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ካልተወገደ እንደ ሀገር ሰላም አናገኘም ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከደጀን እስከ ግንባር በመዝመት አቅም በፈቀደው ሁሉ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽ/ ቤት አደራጅና የስምሪት ቡድን መሪ ሀምሳለቃ ኮሬ ዘመቻ በበኩላቸው ሀገራችን ለሶስተኛ ጊዜ ሳትወድ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በድል እንድትወጣ የተኛውም የውስጥ ችግሮቻችን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን የጋራ ጠላታችን ለመደምሰስ ያሉን አቅም አደራጅተን ከመንግስትና ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን ልንሰለፍ ይገባል ብለዋል ።

የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ሰፊ የሰላም አማራጭ መጠቀም ያልቻለውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ የሀይማኖት አባት ሳይለይ ሁሉም በጋራ ከመንግሥትና ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።

እንደተቋም መደበኛ ሰራዊት የመመልመልና ወደ ግንባር የመላክ ሌሎቹ ተጓዳኝ ተግባራትን ከወትሮ በተሻለ መልኩ ለመፈፀም ተዘጋጅተናል ያሉት ሃምሳለቃ ኮሬ ዘመቻ በግል እንደዜጋ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ሁሉ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *