በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት የተጠቃሚዎችን ምልመላ እያካሄደ ይገኛል።

ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት የተጠቃሚዎችን ምልመላ እያካሄደ ይገኛል።

የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የ2015 ዓ.ም የተጠቃሚዎች መልማይ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች በተመረጡ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የአሰራር ስርዓት እና ፍትሀዊ ስራ ለመስራት የሚያስችላቸው ከየመንደሩ በህብረተሰብ ጥቆማ በተመረጡ አካላት ምልመላ እየተካሄደ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ ምግብ ዋስትና ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ ብዛ ገለፁ።

በከተማችን ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ከገባበት ታህሳስ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመጀመሪያ ዙር 1978 ቤተሰቦች ተጠቃሚ መሆናቸው ያነሱት አቶ መንግሥቱ ፕሮጀክቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በከተማችን ለሶስት ተከታታይ አመት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን በዚህም የቆይታ ጊዜ በከተማው ውስጥ የሚገኙ ስራ አጥ ወገኖችና አቅመ ደካሞች በመለየት በርካታ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን ጠቁመዋል ።

ከእነዚህ ወገኖችም ወደ ስራ ከገቡ በኋላ በየወሩ ከሚከፈላቸው ደመወዝ ላይ 20% እንዲቆጥቡ የሚደረግ ሲሆን የቆይታ ጊዜያቸው ካለቀ በኋላ ከፕሮጀክቱ ከሚሰጣቸው ድጎማ ጋር በማድረግ ራሳቸውን እንዲችሉና ቋሚ ስራ እንዲኖራቸው ይደረጋል ሲሉ አቶ መንግስቱ ገልፀዋል ።

አያይዘውም 2015 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ሶስት ቀበሌዎች አዲስ ህይወት ፣ መናኸሪያና ሰላም በር ቤት ለቤት በመዞር ሁሉም የቀበሌ ነዋሪ ምዝገባ መካሄዱን ገልፀው እስካሁን 3484 የቤተሰብ ሀላፊዎችና በአጠቃላይ 10,374 ቤተሰቦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል ።

በምልመላው ወቅት የነበሩት የሀይማኖት አባት ሐጂ ሚፍታ ያሲን ምልመላው ፍህታዊና ህግና መመሪያው በጠበቀ መልኩ በቀበሌው የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁሉ ባሳተፈ ሁኔታ ምዝገባ እያካሄድን ሲሆን ከነዚህም መካከል የከፋ ችግር ያለባቸውን በቅርበት ስለምናውቃቸው እንዲመዘገቡ እያደረግን ነው ሲሉ ሐጂ ሚፍታ ያሲን ገልፀዋል።

በአካባቢው ከተመረጡ ሽማግሌዎች መካከል አቶ ደንድር ቸገን በበኩላቸው የተመለመሉት የራሳቸው ቤት የሌላቸው (ተከራዮች )፣ ወላጅ አልባ ህፃናት ፣ የመስራት አቅም ኖሯቸው ስራ አጥ የሆኑ ወገኖች በአካባቢው መኖራቸውን ገልፀው ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ ምዝገባው መካሄዱንም አንስተዋል።

በመጨረሻም ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ ቀርበው የሚታዩበት ሁኔታ እንዳለ የወልቂጤ ከተማ ምግብ ዋስትና ቡድን መሪ አቶ መንግስተ ብዛ ገልፀዋል ።

ዘገባው የወ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *