የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ12 ሺህ 621 ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ።

ነሐሴ 26/2014 ዓ. ም

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ12 ሺህ 621 ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው በዘር ከተሸፈነው የስንዴ፣ የገብስና የጤፍ ማሳ 4 ሺህ 969ሄ/ር መሬት በኩታ ገጠም የለማ ሲሆን በዘር ከተሸፈነው ማሳ ከ1 ሚሊዮን 55 ሺህ 536 በላይ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ፅ/ቤቱ አክሎ ገልጿል፡፡

የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የአርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው፡፡
ዘርፉን ለማዘመን መንግስት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከማቅረብ በተጨማሪ በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ በማሳ ዝግጅት፣ በአፈር ማዳበሪያና በምርጥ ዘር አጠቃቀም፣ በአረምና ተባይ ቁጥጥር ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮች የገጠማቸውን የዩሪያ እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመው ምርጥ ዘር 91.35 ኩ/ል ፣ Nps 13059 ኩ/ል ፣ Urea 3159ኩ/ል እንዲሁም ከC1 – C3 ፍንሬሽን ምርጥ ዘር ለአ/አደሩ መሰራጨቱንና ጥቅም ላይ መዋሉን አቶ ሸምሱ ተናግረዋል።

በመሆኑም አርሶ አደሮች ከተለመደውን የአስተራረስ ዘዴ ተላቀው ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ በመጠቀም አሁናዊው የኑሮ ውድነትን ሊያረጋጋ የሚችል ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
በዘንድሮ የመኸር ወቅት 12 ሺህ 621.5 ሄክታር መሬት በማረስ ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

በበልግ እርሻ ልማት 3 ሺህ 333ሄ/ር መሬት በማረስ በበቆሎ፣ በድንች እና በአትክልት ማልማት ተችሏል።
በአጠቃላይ በበልግና በመኸር እርሻ 15 ሺህ 954 ሄ/ር መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን 1ሚሊዮን 950 ሺህ 832ኩ/ል በላይ ምርት ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል።
አርሶ አደሮች ማሳቸውን በመንከባከብ፣ አረምና ተባይ በመቆጣጠርና ግብዓትን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ባለሙያዎች እየሰጡት ያለውን ሙያዊ ድጋፍ አጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የማዳበሪያ ዋጋ ጭማሪና የዩሪያ አቅርቦት እጥረት በመኽር ወቅት ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት ተጠቃሾች መሆናቸውን ጠቅሰው ችግሩን ለመቅረፍም ከዞኑ ግብርና መምሪያ በመነጋገር የአቅርቦት ስራ መሰራቱን ብሎም ቶፕ ድሬሲንግ ላይ ትኩረት በማድረግ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ርብርብ መደረጉን ሃላፊው አክለዋል።

በመጨረሻም አቶ ሸምሱ ባስተላለፉት መልእክት ይህንን ግብ ስኬታማ ለማድረግ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ዘግቧል ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *