የጉራጌ ዞን ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የጉራጌ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ገለፀ ።

ነሐሴ 05/2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የጉራጌ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ገለፀ ።

የጉራጌ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ እንደገለፁት የጉራጌ ዞን ምክርቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብ ላይ በጥልቀት ከተወያየበት በኋላ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጓል።

የዞኑ ምክርቤት በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡ ደስታውን ሲገልጽ በሰላማዊ መንገድ መሆን እንዳለበት አስተባባሪው አሳስበዋል።

የዞኑ ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ የዞኑ ምክርቤት ያጸደቀው በክልል የመደራጀት ውሳኔ መንግስት ምላሽ እስኪሰጥበት ድረስ የዞኑ ህዝብ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የዞኑ ህብረተሰብ የአካባቢውን ሰላም ሲያስጠብቅ እንደነበረ የገለጹት አስተባባሪው እስካሁን በነበረን ቆይታ ከህዝቡ ጋር ተግባብተን ስንሰራ ነበር ። በቀጣይም የአካባቢውን ሰላም እንደሚያስጠብቁ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የውስጥና የውጭ ጠላቶች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ለጸጥታ አካላት መረጃ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ ።

በረጃ ምጭነት ገፃችንን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን!

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *