በ2014 በጀት አመት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ ።

በሐምሌ ወር ብቻ ከ25 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ መክፈላቸውን ጠቁመዋል ።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ እንደገለፁት ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ቀልጣና ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት እና የታክስ ስወራን መቆጣጠር እንዲያስችል የታክስ መመዝገቢያ ማሽኖችንና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል።

በ2014 በጀት አመት 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀው ለዚህ ስኬት የግንዛቤ ማስጨበጫ ፣ የአስተምህሮት ስራውና የህግ ማስከበር ስራው በቅንጅት በመሰራቱ መሆኑን አስረድተዋል ።

ግብር ከፋዮች አላስፈላጊ ቅጣት ውስጥ እንዳይገቡ በተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር 25 ሺህ በላይ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ መክፈላቸውን ጠቅሰው ቀጣይ ባሉት የግብር መክፈያ ወቅት የሒሳብ መዝገባቸውን አሳውቀው በወቅቱ ግብራቸውን በመክፈል ከአላስፈላጊ ቅጣት እንዲድኑ አቶ ሙራድ አሳስበዋል።

በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ መረጃ አሰባሰብ ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያና ቴክኖሎጂ አስተዳደር አስተባባሪ አቶ ወንዳየሁ አድማሱና የህግ ማስከበር አስተባባሪ አቶ ሀይሉ ሸዋረጋ በጋራ በሰጡት አሰሰተያየት የክፍያ ስርአቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ግብር ከፋዩ ግብሩን ባንክ እንዲከፍል እየተሰራ ነው።

በቀጣይም በኢንተርኔት ታክሳቸውን የማሳወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በበጀት አመቱ ህግን የተላለፉ 18 ግብር ከፋዮችን ለህግ በማቅረብም አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ 4ቱ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰጠቱን ተናግረዋል።

በመምሪያው የደምበኞች አገልግሎት ታክስ አሰባሰብና አወሳሰን አስተባባሪ አቶ እንዳለ አድነውና የታክስ ትምህርት ኮሚዩኒኬሽን እና ቅሬታ አጣሪ አስተባባሪ አቶ ይረፉ አባተ ሁለቱም በሰጡት አስተያየት በበጀት አመቱ ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

ለዚህም ስኬት የአስተምህሮት ስራውና የግብር አወሳሰን እና አሰባሰብ ስራው በቅንጅት መሰራቱን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *