የሐዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ ለማድረግ በ20 ሚሊየን ብር የማስፋፊያ ግንባታ እያከናወነ መሆኑ ተገለፀ ።

ከክልል ፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተዉጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የሀዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ጎብኝተዋል።

የሀዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ትዛዙ ፍቃዱ እንዳሉት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች የበቃና የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራትና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር እንዲያደርጉና ሀብት እንዲያፈሩ ያደርጋል።

ኮሌጁ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመፍጠርና ሙሉ በሙሉ በመቅዳት ለኢንተርፕራይዞችና ለአርሶአደሩ ለማሸጋገር እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

እንደ አቶ ትዛዙ ገለጻ ኮሌጁ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ማፍራትና የኢንዱስሪ ኤክስቴንሽ ድጋፍ በማድረግ ማህበረሰቡ በኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት ለወረዳዉ በማቅረብ ረገድ የድርሻዉን እየተወጣ እንደሆነም አስረድተዉ ኢንተርፕራይዞች የሚፈልጓቸዉን ቴክኖሎጂዎችን በማሻሻልና በመቅዳት ለኢንርፕራይዞች ፣ ለህብረተሰቡና ለአርሶአደሩ እያስተላለፉ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የኮሌጁን ግቢ በተለያዩ ችግኞች ከማስዋብ በተጨማሪ ለምግብነት እና ለጥላሁን አገልግሎት የሚውሉ የአቦካዶ ፣ የማንጎና የፓፓያ የመሳሰሉት ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።

በ2013 አመተ ምህረት 39 የአቮካዶ ችግኞች የተተከሉ በ2014 አመተ ምህረት ወደ 40 የአቦካዶ ችግኝና በዚህ አመት ደግሞ ከፍ አድርገዉ በማቀድና በጀት በመመደብና የተከላ ቦታዎችን በማመቻቸት 118 የአቮካዶ ችግኝ መትከላቸዉና ይህም የጽድቅ መጠኑ ወደ 98 ፐርሰንት የሚሆነዉ መጽደቁም አመላክተዋል።

ኮሌጁ በአረንጓዴ ልማት በማስዋብ ረገድ ጥሩ የሚባሉ ስራዎች እያከናወነ እንደሆነም ያመላከቱት አቶ ትዛዙ ይህም በጎ ጅምር ቀጣይነት እንዳለዉም አብራርተዋል።

በኮሌጁ ለብየዳ የሚሆኑ በቂ ማሽኖች መኖሩንም ተናግረዉ እነዚህ ማሽኖች የሚቀመጡበትና ስልጠና ለመስጠት በቂ ሾፕ እንዳልነበረም አስታዉሰዉ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ለክልሉ ፕሮጀክት ቀርጸዉ በመስጠትና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀነጀት 20 ሚሊየን የፈጀ ደረጃዉን የጠበቀ የማስፋፊያ ግንባታ እየተከናወኑ እንደሆነም አብራርተዋል።

የማስፋፊያ ግንባታዉም እስከ መስከረም ወር ድረስ በማጠናቀቅ በ2015 አመተ ምህረት ስልጠና የሚሰጥበት እንደሆነና ሌሎች በግቢ ዉስጥ የማስፋፊያ ግንባታዎች መኖራቸዉ ይህንንም አጠናክረዉ እንደሚያስቀጥሉም አብራርተዋል።

በጉብኝቱ የተገኙ አንዳንድ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ኮሌጁ በመማር ማስተማር ስራዉ የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆን እያከናወነዉ ያለዉን የማስፋፊያ ግንባታ አጋዥ እንደሆነ እንደሆነም ተናግረዋል።

የኮሌጁ ቅጥር ግቢ በተለያዩ የችግኝ አይነቶች ለማስዋብ እየተሰራ ያለዉን ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን ተጭነው ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *